የባህር ከፍታ መጨመር አደጋ እያየለ ነው- ጥናት
አብዛኛዎቹ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የባህር ከፍታ በየ100 ዓመቱ 3 ሜትር ሊደርስ ይችላል
የካርቦን ልቀት መጠን ከቀጠለ የባህር ከፍታ በ2100 እስከ 98 ሴንቲ ሜትር ይጨምራል ተብሏል
የባህር ከፍታ መጨመር አደጋ እያየለ መምጣቱን ጥናትአመላክቷል።
የባህር ከፍታ መጨመር ከአየር ንብረት ለውጥ ትልቁ ስጋቶች አንዱ ሲሆን፤ በሽህዎች ለሚቆጠሩ ደሴቶች መጥፋት እና የባህር ዳርቻዎች መጥለቅለቅ አደጋ ላይ ይጥላል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ቡድን አሁን ያለው የካርቦን ልቀት መጠን ከቀጠለ የባህር ከፍታ በ2100 እስከ 98 ሴንቲ ሜትር እንደሚጨምር አስታውቋል።
ዓለም አቀፍ ተቋማት የዋልታዎች የበረዶ መቅለጥ የባህር ከፍታ መጨመርን ያፋጥነዋል ሲል ስጋታቸውን ይገልጻሉ።
ቀደም ሲል የተደረጉ ጥናቶች ለባህር ጠለል መጨመር ዋናው ምክንያት የበረዶ ሽፋን ላይ ያሉ ትላልቅ ክፍሎች በመጥፋታቸው ምክንያት የአየር ሙቀት መጨመር እንደሆነ ያመላክታሉ።
አብዛኛዎቹ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የባህር ከፍታ በየ100 ዓመቱ ሦስት ሜትር ሊደርስ ይችላል።
ይሁን እንጂ በቅርቡ በአሜሪካ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደ አንድ ጥናት እንዳመለከተው፤ የአንታርክቲካ የበረዶ ንጣፍ መቅለጥ ለባህር ወለል መጨመር ትልቁን ሚና ይጫወታል። ጥናቱ በምድር ምሰሶዎች ውስጥ "መካከለኛ የአየር ንብረት" መረጃዎችን በመተንተን በ 129 እና 116 ሺህ ዓመታት መካከል ባለው በሁለት የበረዶ ዘመን መካከል ባለው ትንታኔ ላይ ተመርኩዞ ነው።
የአንታርክቲካ የበረዶ ንጣፍ ምን ያህል እና መቼ እንደሚቀየር በተመራማሪዎች መካከል ቀጣይነት ያለው ክርክር ቢኖርም፤ ተመራማሪዎች የአንታርክቲካ የበረዶ መቅለጥ ብቻ የባህር ከፍታን ከአንድ ሜትር በላይ ከፍ እንደሚያደርግ ይጠቁማሉ።