ጨዋማነት የባህር ውስጥ ህይወት የሚያጠፋው በምን መንገድ ነው?
የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ወደ ውቅያኖስ ውስጥ ዘልቆ በመግባት በውቅያኖስ ህይወት ላይ ለውጥ እያመጣ ነው
በ1950 እና 2000 መካከል ያለው የባህር ውሃ የጨዋማነት መጠን በ4 በመቶ መጨመሩን ጥናት አረጋግጧል
የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ወደ ውቅያኖስ ውስጥ ዘልቆ በመግባት በውቅያኖስ ህይወት ላይ ለውጥ እያመጣ እና ኑሯቸውን እየረበሸ ነው።
በባህር እና ውቅያኖስ ውስጥ ያሉ ፍጥረታት ከአየር ንብረት ለውጥ አደጋ አላመለጡም። እናም አደጋው ለአየር ንብረት ለውጥ ሳያበረክቱ በመኖሪያቸው እየተመታ ነው።
የውሃ አካላት በዋናነት የሙቀት አማቂ ጋዞችን የመሳብ ሃላፊነት አላቸው ። ነገር ግን የጨው መጠን እየጨመረ ሲሄድ፤ ችግሮች በባህር ውስጥ ያለውን ህይወት ማደናቀፍ ይጀምራሉ።
ባለፈው ሚያዝያ በሳይንስ ጆርናል ላይ የታተመ ጥናት በ1950 እና 2000 መካከል ባለው ጊዜ የባህር ውሃ የጨዋማነት መጠን በ4 በመቶ መጨመሩን አረጋግጧል።
የሙቀት መጠን በሁለት ወይም በሶስት ዲግሪ መጨመር የጨው መጠን ወደ 24ዐበመቶ ሊጨምር ይችላል።
በእያንዳንዱ ጊዜ የሙቀት መጠኑ በአንድ ዲግሪ ሴልሺየስ ሲጨምር፤ የውሃ ዑደት ጨዋማነት ከአምስት እስከ ስምንት በመቶ ባለው መጠን ይጨምራል። በመህኑም በመሬት እና በውሃ አካላት ውስጥ የጨው መጠን ይጎዳል።
የባህር ጨዋማነት ለሁሉም የሚታይ ግልጽ የሆነ አደጋን የደቀነ ነው።
ሁሉም ሰው ስለ የአየር ንብረት ለውጥ እና ከፍተኛ የሙቀት መጠን ያወራል። ነገር ግን ግልጽ አደጋ ስለሆነው ጨዋማነት ማንም ሰው እምብዛም አይናገርም።