በውድድሩ ላይ ብር እና ነሀስ ላመጡ አትሌቶች የገንዘብ ሽልማት እንደሌለ ተገልጿል
በፓሪስ ኦሎምፒክ ወርቅ ያመጡ አትሌቶች 50 ሺህ ዶላር ይሸለማሉ ተባለ፡፡
በየአራት ዓመቱ የሚካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር ዘንድሮም በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ከሀምሌ 19 ቀን እስከ ነሀሴ 5 ቀን 2016 ዓም ካሄዳል፡፡
የሀገርን ሰንደቅ አላማ ከፍ ለማድረግ በሚደረገው በዚህ ውድድር ለይ እስካሁን የገንዘብ ሽልማት ሳይሰጥ ቆይቷል፡፡
በዘንድሮው የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ለይ ለመጀመሪያ ጊዜ የወርቅ ሜዳሊያ ለሚያመጡ አትሌቶች የገንዘብ ሽልማት ይሰጣል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ የወርቅ ሜዳሊያ ለሚያመጡ አትሌቶች 50 ሺህ ዶላር ይሸለማሉ የተባለ ሲሆን ብር እና ነሀስ ለሚያመጡ አትሌቶች ግን የገንዘብ ሽልማት አይሰጥም ተብሏል፡፡
ሁለተኛ እና ሶስተኛ ለሚወጡ አትሌቶች ከአራት ዓመት በኋላ በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ ላይ በሚካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር ላይ ገንዘብ መሸለም እንደሚጀመር በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ዩክሬን ሩሲያ በ2024ቱ የፓሪስ ኦሎምፒክ እንዳትሳተፍ ጠየቀች
ዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ እንዳስታወቀው ከሆነ በፓሪስ ኦሎምፒክ ላይ የወርቅ ሜዳሊያ ለሚያገኙ አትሌቶች 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር በጀት ማዘጋጀቱንም ገልጿል፡፡
በዚህ ውድድር ላይ 48 የወርቅ ሜዳሊያዎች ተዘጋጅተዋልም ተብሏል፡፡
በኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ ለአሸናፊ አትሌቶች የገንዘብ ሽልማት ይሰጥ አይሰጥ የሚለው ጉዳይ እስካሁን ሲያከራክር የቆየ ቢሆንም አሁን ላይ እልባት በማግኘት ላይ እንደሚመስል ተገልጿል፡፡