የሩሲያ ሰንደቅ አላማ በፓሪስ ኦሎምፒክ ላይ ላይውለበለብ እንደሚችል ፕሬዝዳንት ማክሮን ገለጹ
የሩሲያ አትሌቶች በግላቸው እንዲወዳደሩ ሊፈቀድላቸው ይችላል ተብሏል
ዩክሬን ግን የሩሲያ እና ቤላሩስ አትሌቶች በፓሪስ ኦሎምፒክ ላይ ከተሳተፉ ራሴን ከውድድሩ አገላለሁ ብላለች
የሩሲያ ሰንደቅ አላማ በፓሪስ ኦሎምፒክ ላይ ላይውለበለብ እንደሚችል ፕሬዝዳንት ማክሮን ገለጹ።
የፈረንሳይ ዋና ከተማ የሆነችው ፓሪስ ከአንድ ዓመት በኋላ የኦሎምፒክ ውድድሮችን ታስተናግዳለች።
የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት የሆኑት ኢማኑኤል ማክሮን ከዩክሬን ጋር እየተዋጋች ያለችው ሩሲያ በውድድሩ ላይ ላትሳተፍ እንደማትችል ተናግረዋል ።
የሩሲያ እና ቤላሩስ ሰንደቅ አላማዎች በፓሪስ ኦሎምፒክ ላይ ላይውለበለቡ እንደሚችሉ ፕሬዝዳንት ማክሮን ተናግረዋል።
"ሩሲያ በዩክሬን የጦር ወንጀል እየፈጸመች ሰንደቅ አላማዋ በፓሪስ ኦሎምፒክ ሊውለበለብ አይችልም" ያሉት ፕሬዝዳንቱ ዋና ውሳኔው ግን የዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እንደሆነም ተናግረዋል።
አትሌቶቹ በዚህ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ለረጅም ዓመታት ሲለማመዱ የቆዩ እና ምኞታቸው ሊሆን ይችላል በሚል የሀገራቸውን ሰንደቅ አላማ ሳይዙ እንደ ግለሰብ እንዲሳተፉ ሊፈቀድላቸው እንደሚችል ተገልጿል።
ይህም እድል የሚሰጣቸው የሩሲያ ጦርን የሚደግፉ መሆን አለመሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ ይሆናል ሲል ዩሮ ኒውስ ዘግቧል።
ዩክሬን በበኩሏ የሩሲያ እና ቤላሩስ አትሌቶች በፓሪስ ኦሎምፒክ ላይ እንዲወዳደሩ ከተፈቀደላቸው ከውድድሩ ራሷን እንደምታገል ተናግራለች።
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረገች ባለው ጦርነት ምክንያት በርካታ እገዳዎች የተጣሉባት ሲሆን ከቀናት በፊት በሀንጋሪ ቡዳፔስት በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ላይ መታገዷን ተከትሎ በውድድሩ ሳትሳተፍ ቀርታለች።