ጎንደር ዩንቨርሲቲ ያስመረቃቸው ተማሪዎቹ ከ100 ሺህ ማለፋቸውን ገለጸ
ዩንቨርሲቲው የተመሰረተበትን 70ኛ ዓመት እያከበረ ነው
በ70 ዓመታት ውስጥ ልዩ አበርክቶ ላላቸው 10 ሰዎች የክብር ዶክትሬት ሰጥቻለሁም ብሏል ዩንቨርሲቲው
ጎንደር ዩንቨርሲቲ ያስመረቃቸው ተማሪዎቹ ከ100 ሺህ ማለፋቸውን ገለጸ።
በኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ዕጥረት ለመፍታት በሚል በ1947 ዓ.ም መመስረቱ ተገልጿል።
የዩንቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት አጸደወይን እንዳሉት ዩንቨርሲቲው በ70 ዓመት ታሪኩ 100 ሺህ ተማሪዎችን አሰልጥኖ አስመርቋል ብለዋል።
በኢትዮጵያ የሐኪሞች ዕጥረትን ተከትሎ የውጭ ሀገራት የህክምና ባለሙያዎች ወደ ሀገር ውስጥ ይገቡ ይነበረ ሲሆን ጎንደር ዩንቨርሲቲ ይህ ችግር በቋሚነት እንዲፈታ የራሱን አስተዋጽኦ መወጣቱም ተጠቅሷል።
በ1996 ዓ . ም ወደ ዩንቨርሲቲነት ያደገው ጎንደር ዩንቨርስቲ በኢትዮጵያ በተለያዩ የሙያ መስኮች የተሻለ አስተዋጽኦ አድርገዋል ለተባሉ 10 ሰዎች የክብር ዶክትሬት መስጠቱንም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።