ጉግል አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን ለማንቀሳቀስ ከሚጠቀምበት ፕሮሰሰር ጋር በተያያዘ የብዙ ቢሊዮን ዶላር ክስ ቀርቦበታል
ጉግል የኮምፒዩተር ሳይንቲስቶችን የፈጠራ መብት በመጣስ ተከሰ።
ጉግል አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን ለማንቀሳቀስ ከሚጠቀምበት ፕሮሰሰር ጋር በተያያዘ የብዙ ቢሊዮን ዶላር ክስ እንደቀረበበት ሮይተርስ ዘግቧል።
የአልፋቤቱ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጉግል አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስንስን (ኤአይ) ለማንቀሳቀስ የሚጠቀምበት ፕሮሰሰር የኮምፒዩተር ሳይንቲስቶችን የፈጠራ መብት ይጥሳል በሚል ተከሶ በቦስተን የፌደራል ጁሪ ፊት ሊቀርብ ነው ተብሏል።
መቀመጫውን ማሳቹሴት ባደረገው የኮምፒዩተር ሳይንቲስት ጆሴፍ ቤትስ የተቋቋመው ሲንጉላር ኮምፒዩቲን፣ ጉግል የሱን የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂ በመኮረጅ ለኤአይ የጉግል ፍለጋ ፊቸር፣ ለጂሜል፣ ለጉግል ትራስሌት እና ለሌሎች የጉግል አገልግሎቶች ተጠቅሞባቸዋል ብሏል።
የጉግል ክስ እንደሚያመለክተው ሲንጉላር ደርሷል ላለው ጉዳት 7 ቢሊዮን ዶላር እንዲከፈለው ጠይቋል።
የጉግል ኩባንያ ቃል አቀባይ ጆሴ ካስታኔዳ የሲንጉላር ክስ "ተንኮሎ ያዘለ" ነው፤ ጉግል የራሱን ፕሮሰሰር አልምቶ ለበርካታ አመታት ሲጠቀም ነበር ብሏል።
ቃል አቀባዩ "ፍርድ ቤት ቀርበን ሀቁን እናስረዳለን" ብሏል።
የሲንጉላር ጠበቃ ምላሽ አልመስጠቱን ዘገባው ጠቅሷል።
ሲንጉላር በ2019 ያቀረበው ቅሬት እንደጠቀሰው ቤትስ የኮምፒዩተር ፕሮሰሲንግ ፈጠራዎቹን ከ2010-2014 ባለው ጊዜ ውስጥ ለጉግል አጋርቷል። ሲንጉላር እንደገለጸው የጉግልን የኤአይ አቅም የሚያሳድገው ቴንስር ፕሮሰሲንግ ዩኒት ከቤትስ ቴክኖሎጂ የተኮረጀ እና ሁለት የፈጠራ መብቶችን የሚጥስ ነው።
ጉግል በ2016 አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን በማንቀሳቀስ ንግግር ለመለየት፣ ይዘት ለማዘጋጀት እና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውል የራሱን ፕሮሰሲንግ ዩኒት አስተዋውቆ ነበር።