የጎግል ኪሳራ በታሪክ አምስተኛው ከፍተኛ መጠን ያለው ኪሳራ እንደሆነ ተገልጿል
የጎግል እናት አልፋቤት ኩባንያ 166 ቢሊዮን ዶላር መክሰሩ ተገለጸ፡፡
የአሜሪካው የቴክኖሎጂ ኩባንያ አልፋቤት በሰዓታት ውስጥ የ166 ቢሊዮን ኪሳራ እንደገጠመው ተገልጿል፡፡
ከጠቅላላ የኩባንያው አክስዮን ውስጥ የ10 በመቶ ቅናሽ ያጋጠመው አልፋቤት ኩባንያ ኪሳራው የገጠመው የገቢ ሪፖርቱን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ እንደሆነ ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
የአልፋቤት ኩባንያ ኪሳራ እንደ ናይክ እና ዲስኒ አይነት ኩባንያዎች ጠቅላላ ሀብት መጠን አለውም ተብሏል፡፡
በጎግል ማፕ ምክንያት ባሏ የሞተባት ሚስት ጎግልን ከሰሰች
የአልፋቤት ኩባንያ የገንዘብ ኪሳራ በአሜሪካ ኪሳራ መጠን አምስተኛው ከባድ ኪሳራ ነው ተብሏል፡፡
የጎግል እናት ኩባንያ አልፋቤት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 434 ሚሊዮን ዶላር ገቢ የማግኘት እቅድ የነበረው ሲሆን ያገኘው ትርፍ ግን 266 ሚሊዮን ዶላር ብቻ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ይሁንና የጎግል ዋነኛ ተፎካካሪ የሆነው ማይክሮሶፍት ኩባንያ የተሸለ ትርፍ አግኝቷል የተባለ ሲሆን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን በሚገባ አለመጠቀሙ ለኪሳራ ሳይዳርገው እንዳልቀረም የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ግምታቸውን ሰጥተዋል፡፡
የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የሆኑት አሜሪካዊው ኢሉን መስክ ባሳለፍነው ሳምንት በአንድ ቀን 16 ቢሊዮን ዶላር መክሰራቸው ይታወሳል።
ባለጸጋው ኪሳራው የደረሰባቸው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪን በማምረት የሚታወቀው ቴስላ ኩባንያ የአክስዮን ዋጋ በመቀነሱ ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።