ሁዋዌ ‘ሀርመኒ’ የተባለ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ስራ ላይ አዋለ
የስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች ኦፕሬቲንግ ሲስተማቸውን ወደ አዲሱ ‘ሀርመኒ’ ኦፕሬቲንግ ሲስተም መቀየር ይችላሉ
አዲሱ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከአንድሮይድ እና አይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች የተለየ ነው
የቻይናው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሁዋዌ አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን መጠቀም አቆመ፡፡
ህዋዌ ‘ሀርመኒ’ የተሰኘ የራሱን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከትናንት ጀምሮ ወደ ስራ ማስገባቱን አስታውቋል።
አዲሱ የሁዋዌ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ከትናት ምሽት ጀምሮ በርከት ላሉ የስማርት ስልክ ሞዴሎች መልቀቅ መጀመሩም ተነግሯል።
በዚህም ሁዋዌ አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ስልኮች የሚጠቀሙ ሰዎች ኦፕሬቲንግ ሲስተማቸውን ወደ አዲሱ ‘ሀርመኒ’ ኦፕሬቲንግ ሲስተም እንዲቀይሩ እድል ሰጥቷል።
ሁዋዌ ‘ሀርመኒ’ የተባለ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ይፋ ማድረጉ ከዚህ በኋላ የአሜሪካ ምርት ከሆነው የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ጥገኝነት የሚገላግለው ሆናልም ተብሏል።
የቻይናው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሁዋዌ የስማርት ስልክ ገበያውን ከጎዳው የአሜሪካ የኢኮኖሚ ማእቀብ ለማገገም እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል።
የአሜሪካ ማእቀብ ጎግል አልፋ ቤት ግሩፕ ለአዳዲስ የሁዋዌ ስማርት ስልክ ሞዴሎች የቴክኒክ ድጋፍን እንዳይሰጥ የሚከለከል መሆኑ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎም ሁዋዌ አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለመተካት የሚያስችለውን አማራጭ የራሱን ኦፕሬቲንግ ሲስተም መስራት መጀመሩም ይታወሳል።
አዲሱ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከአንድሮይድ እና አይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች የተለየ መሆኑን ሁዋዌ አስታውቋል።
‘ሀርመኒ’ የተባለውን ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማንኛውም ስማርት ስልክ ላይ መገልገል እንዲቻል ተደርጎ መሰራቱም ነው የተገለፀው።