በአሜሪካ የሚገኙ ጉሬላዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው
በጆርጂያ እንስሳት ማቆያ ካሉ 20 ጉሬላዎች 13ቱ በኮቪድ ተይዘዋል
ቫይረሱ የተገኘባቸው ጉሬላዎች እንዲያገግሙ ክትትል እየተደረገላቸው ነው ተብሏል
በአሜሪካ የሚገኙ ጉሬላዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።
በአሜሪካ ጆርጂያ ግዛት በእንስሳት መጠለያ ወይም (ዙ) ውስጥ የነበሩ ጎሪላዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ተገልጿል።
በዚህ እንስሳት መጠለያ ውስጥ 20 ጎሪላዎች ይኖሩ የነበረ ሲሆን ከዚህ ወስጥ 13ቱ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ግርምትን ፈጥሯል።
የጎሪላዎቹ ተንከባካቢዎች የኮሮና ቫይረስ ከትባት የተከተቡ እና በቫይረሱ ላለመጠቃታቸው ተገቢው ምርመራ ተደርጎ እያለ እንዴት እንስሳቱ በዚሁ ቫይረስ ሊጠቁ ቻሉ በሚል ምርመራ በመካሄድ ላይ መሆኑን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።
ይህ እንዳለ ሆኖ ግን ቫይረሱ የተገኘባቸው ጎሪላዎች ከቫይረሱ እንዲያገግሙ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑ ዘገባው አክሏል።
የጎሪላዎቹ ናሙናም የተሻለ መርመራ እንዲደረግላቸው ወደ ብሔራዊ የእንስሳት ቤተሙከራ አገለግሎት ተልኳል ተብሏል።
ጉሬላዎቹ በቫይረሱ ሊጠቁ የቻሉት በእንስሳት መጠለያው ወስጥ በሚሰሩ ሰራተኞች ሊሆን የችላል የሚል ግምት በመሰጠት ላይ ቢሆንም እነዚህ ሰራተኞች ማስክ እና ሌሎች ቫይረሱ እንዳይሰራጭ የሚከላከሉ መሳሪያዎችን እየተጠቁ መሆኑ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል።
በእንስሳቱ ላይ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የተደረገላቸው አንድ የ60 ዓመት እድሜ ያለው ጉሬላ የኮሮና ቫይረስ ምልክት ማሳየቱን ተከትሎ ነበር።
በቫይረሱ የተጠቁት ጉሪላዎች እንዳገገሙ ለእንስሳቱ የተዘጋጀ የኮቪድ ክትባት ጎሪላዎቹን ጨምሮ በመጠለያ ጣቢያው ያሉ ነብሮች እና አንበሳዎችም እንደሚከተቡ ተገልጿል።
ከዚህ በፊት ድመት እና ውሻዎች በኮሮና ቫይረስ እንደሚጠቁ በምርመራ መረጋገጡ ይታወሳል።