መንግስት የምክርቤት አባላትን ጨምሮ 23 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ
መንግስት ሁለት የምክርቤት አባላትን ጨምሮ 23 ሰዎችን ከአማራ ክልሉ ግጭት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል
የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአዲስ አበባ ምክርቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ካሳ ተሻገር ከታሰሩት ውስጥ መሆናቸውን መንግስት ገልጽ አድርጓል።
መንግስት የምክርቤት አባላትን ጨምሮ 23 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ሁለት የምክርቤት አባላትን ጨምሮ 23 ሰዎችን በአስቸኳይ አዋጁ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን(አብን) በመወከል የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ እና ብልጽግና ፖርቲን በመወከል የአዲስ አበባ ምክርቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ካሳ ተሻገር ከታሰሩት ውስጥ መሆናቸውን መንግስት ግልጽ አድርጓል።
የአገልግሎቱ ሚኒስቴር ለገሰ ቱሉ በአማራ ክልል የታወጀው አስቸኳይ አዋጁ የመጀመሪያ ምዕራፍ መጠናቀቁን እና በግጭት ውስጥ የነበሩ ከተሞች ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሳቸውኖ ገልጸዋል።
"የህግ ማስከበር" ዘመቻው እንደሚቀጥል የገለጹት ሚኒስትሩ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረማርቆስ፣ ደብረብርሃን፣ ላሊበላ፣ ሸዋሮቢት ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሳቸውን ተናግረዋል።
የፌደራል መንግስት ባለፈው ሚያዝያ ወር የክልል ልዩ ኃይሎችን ለማፍረስና መልሶ ለማደረጃት መወሰኑን ተከትሎ በአማራ ክልል ያለው የጸጥታ ችግር እየተባባሰ መጥቷል።
በክልሉ የተነሳውን አለመረጋጋት በመደበኛ የጸጥታ መዋቅር መፍታት አልተቻለኝም ያለው መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አውጇል።
በመንግስት የጸጥታ ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተቀሰቀው ግጭት ንጹሃን ሰዎች እንዲጎዱ እና የሀገር አቋራጭ ትራንፖርት እንዲስተጓጎል አድርጓል።
የተመድ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ትናንት ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል እየተባባሰ የመጣው ሁኔታ በጽኑ እንደሚያሳስበው ገልጿል።