የሱዳን መንግስትና አማጺያን የመጨረሻውን የሰላም ስምምነት በጁባ ተፈራረሙ
በፈረንጆቹ 2003 በዳርፉር ብቻ በተካሄደ ውጊያ 300ሺ ያህል ሰዎች ተገድለዋል
ከአልበሽር ውድቀት በኋላ ሀገሪቱን የተቆጣጠረው መንግስት ከአማጺያን ጋር ስምምነት መድረስን ቀዳሚ ተግባር አድርጎ ሲንቀሳቀስ ነበር
ከአልበሽር ውድቀት በኋላ ሀገሪቱን የተቆጣጠረው መንግስት ከአማጺያን ጋር ስምምነት መድረስን ቀዳሚ ተግባር አድርጎ ሲንቀሳቀስ ነበር
የሱዳን የሽግግር መንግስትና የሪቮሉሽናሪ ግምባር ጥምረት የመጨረሻውን የሰላም ስምምት የተለያዩ ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ፤ከአፍሪካና ከሱዳን የተውጣጡ ተወካዮች በታደሙበት በደቡብ ሰዱን ተፈራርመዋል፡፡
የሪቮሉሽናሪ ጥምረቱ በብሉ ናይልና ሳውዝ ኮርዶፋን የሚንቀሳቀሰው ሪቮሊሹበናሪ ግንባርና አጋር የሆነው ሪቮሉሽናሪ ጥምረት ሃይል፣ በሚኒ አርኮ ሚናዊ የሚመራው የሱዳን ሊብሬሽን ሞቭመንትና በጅብሪል ኢብራሁም የሚመራው የፍትህና እኩልነት ሞቭመንትና በሃዲ እድሪስ ያሂያ የሚመራው የሰዱን ላይብሬሽን ሞቭመንት የሽግግር ምክርቤትን ያካትታል፡፡
ጥምረቱ በማሊክ አጋር የሚመራውን የሱዳን ህዝብ ሊብሬሽን ሞቭመንትም በጁባው ስምምነት ተካተዋል፡፡ በሪቮሉሽናሪ ጥምረቱ ውስጥ በምስራቅ፣በማእከላዊና በሰሜን የሚገኙ አካላት በስምምነቱ ተካተዋል፡፡
የሱዳን የረጅም ጊዜ መሪ ኦማር አልበሽር፣ ለወራት የዘለቀውን ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ፣ እ.አ.ኤ. ሚያዚያ 2019 ከስልጣን ሲወገዱ ወደ ኃላፊነት የመጣው የሱዳን የሽግግር መንግስት ከዓማጺያን ቡድኖች ጋር የሰላም ስምምነት ላይ መድረስን ቀዳሚ ተግባሩ አድርጎ ሲሰራ ቆይቷል፡፡
ስምምነቱ በዋነኝነት በፀጥታ ፣ በመሬት ባለቤትነት ፣ በሽግግር ፍትህ ፣ በስልጣን ማጋራት እና በጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የተሰደዱ ሰዎችን መልሶ ማቋቋም ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በተጨማሪም የአማጺ ኃይሎችን ማፍረስ እና ተዋጊዎቻቸውን ወደ ብሔራዊ ጦር ስለማቀላቀልም ይመለከታል፡፡
በፊርማ ስነ ስርአቱ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ፣የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሐማት፣ የኢትዮጵያ፣ የጅቡቲ፣ የሶማሊያ፣የቻድ ፕሬዚዳንቶች ፤ የግብጽ ጠቅላይ ሚኒስትርና ሌሎችም ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡
በፈረንጆቹ 2003 አማጺያን መሳሪያ ካነሱ በኋላ በዳርፉር ብቻ በተካሄደው ውጊያ 300ሺ ያህል ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
በፈረንጆቹ ከጥቅምት 2019 ጀምሮ ደቡብ ሱዳን በሱዳን መንግስት እና በዳርፉር፣ ደቡብ ኮርዶፋን እና ብሉ ናይል ግዛቶች በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖች መካከል ሽምግልና ስታደርግ ቆይታለች፡፡