ሩሲያ የዩክሬን መሰረት ልማቶች ላይ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ የእህል ዋጋ ጭማሪ አሳየ
ሩሲያ በዩክሬን ዋና ዋና ከተሞች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት መክፈቷን ገለጸች
የሩሲያ ጥቃት ከዩክሬን የእህል ምርት እንዲላክ የተደረሰውን ስምምንት እንዳያስተጓጉል ተሰግቷል
ሩሲያ የዩክሬን መሰረት ልማቶች ላይ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ በዓለም ገበያ የእህል ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ ያሳየ መሆኑ ተገለፀ።
ባሳለፍነው ቅዳሜ ክሪሚያ ግዛትን ከተቀረው ሩሲያ ጋር የሚያተሳስረው ዋና ድልድይ በዩክሬን መመታቱን ተከትሎ ሩሲያ በትናትናው ዩክሬን መሰረተ ልማችን ኢላ ያደረገ ጥቃት መሰንዘር ጀምራች።
የሩሲያ መከላከያ ባወጣው መግለጫ የዩክሬንን ወታደራዊ እና የሀይል መሰረተ ልማት ትኩረት ያደረጉ የሚሳኤል ጥቃቶችን ሰንዝራለች።
ጥቃቱን ተከትሎ በዩክሬን መዲና ኪየቭን ጨምሮ በርካታ የዩክሬን ከተሞች በሩሲያ ሚሳኤል ጥቃቶችን ያስተናገዱ ሲሆን ዩክሬን በበኩሏ በርካታ ንጹሃን በሩሲያ ሚሳኤል መገደላቸውን አስታውቃለች።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ እንዳዲስ የከፈተችውን ጥቃት ተከትሎም በዓለም ገበያ የእህል ምርቶች ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ እያሳየ መሆኑን አር.ቲ ዘግቧል።
ለአብነትም በትናትናው እለት ብቻ በአሜሪካዋ ችካጎ የዓለም ገበያ የስንዴ ዋጋ የ4 ነጥብ 4 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱ ተነግሯል።
ከእህል ዋጋ መጨመር በተጨማሪም በከወራት በፊት በቱርክ እና በተባሩት መንግስታት ድርጅት አመቻችነት ተጀመሮ የነበረው ከዩክሬን የእህል ምርቶችን የመላክ ስራ ሊስተጓጎል ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።
ዩክሬን የኔቶ አባል እሆናለሁ ማለቷን ከሩሲያ ጋር ወደለየለት ጦርነት ከገባች ሰባት ወራት ያስቆጠረች ሲሆን ይህ ጦርነት በርካታ ጉዳቶች አስከትሏል።
ሩሲያ ለልዩ ዘመቻ በሚል ወደ ዩክሬን ምድር ጦሯን ካስገባች በኋላ ዓለማችን በርካታ ክስተቶችን ያስተናገደች ሲሆን የዓለም ምግብና ነዳጅ ዋጋ መጨመር፣ ከ10 ሚሊዮን በላይ ዩክሬናዊያን ወደ ጎረቤት ሀገራት መሰደድ እና ሌሎችም ዋነኛ የዓለማችን ክስተቶች ናቸው።