ይህ ዓለም አቀፍ የስርቆት ቡድን የነዳጅ ምርቶችን በስውር ሲሸጥ እንደነበር ተገልጿል
በ21 ቢሊዮን ዶላር ዘረፋ የሚፈለገው ተጠርጣሪ በግሪክ ተያዘ፡፡
ሮይተርስ የግሪክ ባለስልጣናትን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ ተጠርጣሪው በላቲን አሜሪካ የሚመረቱ የነዳጅ ምርቶችን ለዓለም ገበያ ሲያቀርብ ነበር፡፡
የጣልያን ዜግነት አለው የተባለው ይህ ተጠርጣሪ በዋቀረው የላቲን አሜሪካ ነዳጅ ምርቶች ዘራፊ ቡድን አማካኝነት ለዓለም ገበያ በህገወጥ መንገድ ሲያቀርብ እንደነበር በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
በድምሩ 21 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ እንዳገኘ የተገለጸው ይህ ተጠርጣሪ በዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖል አማካኝነት የእስር ማዘዣ ወጥቶበት ነበርም ተብሏል፡፡
የግሪክ ፖሊስም በዚህ የኢንተርፖል የእስር ማዘዣ አማካኝነት በግሪክ መዲና አቴንስ ከተማ ውስጥ እንደተያዘ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ተጠርጣሪው በተለይም የቬንዙዌላ እና ሌሎች የደቡብ አሜሪካ ሀገራት ነዳጅን በዘረጋው ህገወጥ የዝርፊያ ሰንሰለት አማካኝነት ለዓለም ገበያ ሲያቀርብ እና ሀብት ሲሰበስብ እንደቆየም ተገልጿል፡፡
የቀድሞው የሐዋሳ ከንቲባ ጠባቂ በጠለፋ ወንጀል የ16 ዓመት እስር ተፈረደበት
በአቴንስ የተያዘው ይህ ተጠርጣሪ ለቬንዙዌላ መንግስት ተላልፎ ሊሰጥ ይችላል የተባለ ሲሆን በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎች እስካሁን አልወጡም፡፡
ለጊዜው ስሙ ያልተጠቀሰው የ47 ዓመቱ ይህ ተጠርጣሪ በተለይም ለዓለም ገበያ ሊቀርቡ በወደቦች ላይ የተከማቹ የነዳጅ ምርቶችን በማጭበርበር ወደ ሌሎች ሀገራት ሲልክም ነበር ተብሏል፡፡
የእስያ ሀገራት ዋነኛ የዚህ ዘራፊ ቡድን ገዢ እና ተባባሪ ሀገራት ናቸው የተባለ ሲሆን የሀገራቱ ስም እስካሁን አልተጠቀሰም፡፡