"አረንጓዴ ሃይድሮጂን ለአፍሪካ የመዳን መንገድ ነው"- ማህሙድ ሞሂልዲን
አፍሪካ የንጹህ ኃይል ዘላቂነትን ለማረጋገጥ ኢንቨስት ማድረግ አለባት ተብሏል
በአቢጃን በተካሄደው የአፍሪካ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ፎረም ላይ አረንጓዴ ሃይድሮጂን ለአህጉሪቱ ያለውን ጠቀሜታ ላይ ስምምነት ተደርሷል
በተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ኮፕ 27 ተወካይ ዶ/ር ማህሙድ ሞሂልዲን አፍሪካ ፊቷን ወደ ሃይድሮጂን ልማት ማድረግ አለባት ብለዋል።
ፍላጎትን በመጨመር እና የምርት፣ የመጓጓዣ እና የማከማቻ ወጪዎችን በመቀነስ አረንጓዴ ሃይድሮጂንን ማምረት እና ወደ ውጭ የመላክ አዋጭነት ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህን ያሉት በአይቮሪኮስት ርዕሰ መዲና አቢጃን በተደረገው የአፍሪካ ዋና ስራ አስፈጻሚዎች ፎረም ላይ ነው።
ሞሂልዲን የአፍሪካ ሀገራት በአረንጓዴ ሃይድሮጂን መስክ ተስፋ ሰጪ ሀገራዊ እና ክልላዊ ተነሳሽነት እንዳላቸው ገልጸው፤ ነገር ግን ተስፋውን እውን ለማድረግ ያሉባቸውን ችግሮች ለመቅረፍ የቁጥጥር ማዕቀፎችን እና የድርጊት መርሆች ያስፈልጋቸዋል ብለዋል።
ሞሂልዲን የአፍሪካን ምርት እና የአረንጓዴ ሃይድሮጂን ክምችት ፍላጎት ለመጨመር እና የአጎራባች ሀገራት እና ክልሎች ፍላጎት እንደ እድል ለመጠቀም ከከባቢ ጋር ተስማሚ ነዳጅ በቂ አንደሚሆን አሳስበዋል።
ለአረንጓዴ ሃይድሮጂን ምርት የመሰረተ ልማትን ለማሳደግ እና የአቅርቦት ሰንሰለት ድጋፍን ለማሳደግ ይሰራልም ሲሉ አክለዋል።
ይህን የንጹህ ኃይል ምንጭ ቀጣይነት እና ዘላቂነትን ለማረጋገጥ አፍሪካ የሰው ሀብት ላይ ኢንቨስት ማድረግ፣ ማሰልጠን እና ከአረንጓዴ ሃይድሮጂን ምርት ጋር የተያያዘ የላቀ ቴክኖሎጂ ማቅረብ አለባት ብለዋል።