ከ150 በላይ ድርጅቶች ፕሬዝዳንት ባይደን ጓንታናሞን እንዲዘጉ አሳሰቡ
የጓንታናሞ ቤይ እስር ቤት ከተከፈተ 21 ዓመታትን በማሰብ ተሟጋቾች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል
ድርጅቶቹ ያለ ክስ እና ፍትኃዊ ፍርድ ለሁለት አስርት ዓመታት በእስር ላይ በቆዩት ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት እንዲቆም ወትውተዋል
ከ150 በላይ ድርጅቶች ፕሬዝዳንት ባይደን ጓንታናሞን እንዲዘጉ አሳሰቡ
ከ150 የሚበልጡ ድርጅቶች ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን “በኩባ ጓንታናሞ ቤይ የሚገኘውን የእስር ቤት ለመዝጋት ቅድሚያ ይስጡ” የሚል ደብዳቤ ልከዋል።
ደብዳቤው የተፈረመው ከአሜሪካና ከሌሎች ሀገራት በተውጣጡ 159 ድርጅቶች ሲሆን፤ ራሳቸውን "የተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ቡድን" ብለው የሚጠሩት በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች፣ የስደተኞች መብት፣ የዘር ፍትህ እና ጸረ-ሙስሊም መድልዎ በመዋጋት ላይ የተሰማሩ ናቸው ተብሏል።
"አሜሪካ ለሰብዓዊ መብትና ደህንነት መጠበቅ አካሄዷን ለማስተካከል ጊዜው አልፎባታል። ድህረ 9/11 ካስከተለው ጉዳት ጋር ትርጉም ያለው ስሌት በማድረግ ለለውጡ ጊዜው አልፏል። የጓንታናሞ ማቆያ ቦታን መዝጋት፣ የታሰሩትን መፍታት፣ ወታደራዊ እስራት ማቆም እና ወታደራዊ ሰፈሩን በህገ-ወጥ መንገድ ለማሰር በጭራሽ መፈቀድ የለበትም። እነዚህ አስፈላጊ እርምጃዎች ናቸው” ሲሉ በደብዳቤው ጽፈዋል።
"ያለ ክስ እና ፍትኃዊ ፍርድ ለሁለት አስርት ዓመታት በእስር ላይ በቆዩት ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት በማሰብ ሳትዘገዩ እንድትሰሩ እናሳስባችኋለን" ሲሉም አክለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከመስከረም 11 ቀን 2001 ከተፈጸመው የአሸባሪዎች ጥቃት በኋላ በአፍጋኒስታን፣ ኢራቅ እና ሌሎች ቦታዎች የሽብር ተጠርጣሪዎችን በመያዝ የሚያስረው የአሜሪካ ወታደራዊ እስር ቤት ጓንታናሞ ቤይ ከተከፈተ 21 ዓመታትን በማስመልከት ምናባዊ ሰልፍ ተካሄዷል።
በዝግጅቱ ላይ አሜሪካ ከኩባ የተከራየችው ታዋቂ እስር ቤት እንዲዘጋ የጠየቁት አንቂዎች፣ ጠበቆች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን መሆናቸውን አናዶሉ ዘግቧል።