በዚህ ተመሳሳይ ዓመት 323 ፖሊሶች መገደላቸው ተገልጿል
የአሜሪካ ፖሊስ በ2022 ዓመት በታሪክ ብዙ ሰው መግደሉ ተገለጸ።
የዓለማችን ልዕለ ሀያል በሆነችው አሜሪካ ከቀናት በፊት በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2022 ዓመት ፖሊስ በታሪክ ብዙ ሰዎች የገደለበት ዓመት ሆኗል ተብሏል።
- በአሜሪካ በካፒቶል ሁከት የሞተ ፖሊስ ቤተሰቦች 10 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፈላቸው ከሰሱ
- 90 በመቶ አሜሪካዊያን በሀገራቸው የፖለቲካ ግጭት ይከሰታል ብለው እንደሚያምኑ ጥናት አመለከተ
እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በ2022 ዓመት 1 ሺህ 176 አሜሪካዊያን በፖሊስ የተገደሉ ሲሆን ይህም በታሪክ ከፍተኛው እንደሆነ ተገልጿል።
በዚህ ዓመት በፖሊስ የተገደሉት ሰዎች በ2021 ዓመት ከተገደሉት ጋር ሲነጻጸር በ31 ብልጫ እንዳለው ዩኤስ ኒውስ አስነብቧል።
ፖሊስ ከጥቂት ቀናት በስተቀር በየዕለቱ ንጹሀንን ይገድላል የተባለ ሲሆን በአሜሪካ ሰዎች ያልተገደሉባቸው ቀናት 13 ቀናት ብቻ እንደሆኑም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
በአሜሪካ ከሶስቱ ተገዳዮች ውስጥ አንዱ ከፖሊስ ለመሸሽ ሲሞክሩ እንደሚገደሉ የጥቁሮች ህይወት ያገባናል የተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት ያስጠናው ጥናት ያስረዳል።
ይህ በዚህ እንዳለ በዚሁ በተጠናቀቀው 2022 ዓመት 323 ፖሊሶች ህግ በማስከበር ላይ እያሉ ህይወታቸው እንዳለፈ ተጠቁሟል።