የቀድሞው ፕሬዘዳንት ትራምፕ በ2016 የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የጓንታናሞ ባይ እስርቤትን በስራ ላይ እንደሚቆይና በ “መጥፎ ሰዎች” እንደሚሞላ ገልጸው ነበር
ኋይት ኃውስ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን የስልጣን ዘመናቸው ከማብቃቱ በፊት በሽብር የተጠረጠሩ ግለሰቦች የሚታሰሩበትን የጓንታናሞ ባይ እስርቤትን የመዝጋት አላማ እንዳላቸው አስታውቋል፡፡
መቼ ይዘጋል ተብሎው በጋዜጠኞች የተጠየቁት የኋይት ኃውስ ፕሬስ ሴክሬታሪ“ያ እርግጠኛ ግብ ነው፤ ፍላጎታችን ነው” የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡ፕሬስ ሴክሬታሪዋ እንዳሉት አስተዳደሩ የባይደን አስተዳደር ያለበት መጫውቻ ምን እንደሚመስልና ከበፊቱ አስተዳደር ምን ወርሷል የሚለውን ለማወቅ ዳሰሳ እየተካሄደ ነው ብለዋል፡፡
የቀድሞው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፈረንጆቹ 2016 በተካሄደው የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የጓንታናሞ ባይ እስርቤትን በስራ ላይ እንደሚቆይና “በመጥፎ ሰዎች” እንደሚሞላ ገልጸው ነበር፡፡ ከትራምፕ በፊት በነበሩት ባራክ ኦባማ ጊዜ እስረኖች እንደሚለቀቁ ቃል ተገብቶላቸው ነበር፤ ነገርግን ኦባማ የኮንግረሱን ፍቃድ ስላላገኙ እስረኞቹ መፈታት አልተሳካም፡፡
ፕሬዘዳንት ባይደን በኦባማ ጊዜ ምክትል ፕሬዘዳንት ነበሩ፡፡
በአሜሪካ ሴፕቴምበር 11 የተከሰተውን ከባድ አቀናብሬያለሁ ብሎ ኃላፊነት የወሰደውን ፓኪስታናዊ ካሊድ ሸህ መሃመድን ጨምሮ ከ”ዋር ኦን ቴረር” ጋር ግኝኑነት ያላቸው ፍረደኖች በወታደራዊው እስርቤት ይገኛሉ፡፡
እስርቤቱ እስካሁን 40 እስርኞች የሚገኙበት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 26ቱ አደገኞች ናቸው ተብለው የማይለቀቁና የፍርድ ሂደቱም ነገሩ ውስብስብ ስለሆነ የተጓተተባቸው ናቸው፡፡
ከ9/11 ጥቃት በኋላ በፕሬዘዳንት ጆርጅ ቡሽ ስር የነበረው የአሜሪካ ጦር በምስራቅ ኩባ ጫፍ በሚገኘው የአሜሪካ ናቫል ቤዝ እስርቤቱ ተገንብቷል፡፡