ጊኒ የኢቦላ ወረርሽኝ አዋጅ ስታውጅ፣ሴራሊዮን የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ለመስጠት ተዘጋጅታለች
አዋጅ አለምአቀፍ የጤና መመሪያዎች ጋር በሚጣጣም መልኩ ነው ተብሏል
ምእራብ አፍሪካዊቷ ጊኒ አዋጅ ያወጀችው ሶስት ሰዎች በኢቦላ ቫይረስ ምክንያት መሞታቸው ከተረጋገጠ በኋለ ነው
ምእራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ጊኒ ሶስት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ተመርምረው በኢቦላ ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠና ሌሎች አራት ሰዎች ከታመሙ በኋላ ሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለች፡፡
ይህ ክስተት አለም በፈረንጆቹ ከ2013 እስከ 2016 ከተከሰተው አደገኛ ወረርሽኝ በኋላ የመጀመሪያ መሆኑ ተዘግቧል፡፡ ሌሎች አራት ሰዎች በቀብር ላይ ከተገኙ በኋላ የማስመለስና የመድማት ምልክት አሳይተዋል፡፡
የጊኒ ጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ “በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነን በአለም አቀፍ የጤና መመሪያዎች መሰረት የኢቦላ ወረርሽኝ መከሰቱን አውጇል” ብሏል፡፡ በፈረንጆቹ በ2013 እስከ 2016 የተከሰተው ወረርሽኝ እንቅስቃሴ በበዛበት ኒዘርኮር መከሰቱ ቫይረሱን ለመከላከል የነበረውን ጥረት አውኮት ነበር፡፡ በቫይረሱ 11 300 ሰዎች ገደለ ሲሆን አብዛኖቹ የጊኒ፣የላይቤሪያና ሴራሊዮን ዜጎች ናቸው፡፡
ሌላኛዋ የምእራብ አፍሪካ ሀገር ሴራሊዮን በጎረቤት ጊኒ ሰባት ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ በሽታውን ለመከላከል ዝግጅት አድርጋለች፡፡ የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በፈረንጆቹ 2014-15 ኢቦላን ለመቆጣጠር የተቋቋመው መዋቅር መኖሩን አስታውቋል፡፡
መግለጫው ሴራሊዮን ባለሙያዎቿንና ልምዷን ያዘጋጀች ሲሆን ይህም ቫይረሱ እንደገና ወደ ሀገሪቱ እንዳይገባ ብቻ ሳይሆን ለሁሉንም ዜጎች ህይወት ለመጠበቅ ጠንካራ የጤና ስርአት መገንባቱን ጠቅሷል፡፡