በጊኒ ዕሁድ ዕለት ከተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በኋላ በፖሊስና በተቃዋሚዎች መካከል በተፈጠረ ሁከት ሰባት ሰዎች መሞታቸው ገለጸ
በጊኒ ዕሁድ ዕለት ከተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በኋላ በፖሊስና በተቃዋሚዎች መካከል በተፈጠረ ሁከት ሰባት ሰዎች መሞታቸው ገለጸ
በጊኒ ዕሁድ ዕለት ከተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በኋላ በፖሊስና በተቃዋሚዎች መካከል በተፈጠረ ሁከት ሰባት ሰዎች መሞታቸውንና ብዙዎች መጎዳታቸውን የሀገሪቱ የደህንነት እና ሲቪል ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስትሩ አልበርት ዳማንታንግ እንደገለጹት በኮናክሪ በሚገኙ ሁለት ሆስፒታሎች አራት ሰዎች መሞታቸውን ሪፖርት መደረጉን ሲጅቲኤን ዘግቧል፡፡ ከዋና ከተማዋ ኮናክሪ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ደግሞ አንድ ግለሰብ በመረጋገጥ ህይወቱ ሲያልፍ ሁለቱ ደግሞ በጥይት ተመተው መሞታቸው ነው የተዘገበው፡፡
ሚኒስትሩ አንድ የፖሊስ አባል መገደሉን እና ሌላ አባል ደግሞ በነበረው ሁከት ተረጋግጦ ጉዳት እንደደረሰበት አስታውቀዋል፡፡
በተፈጠረው ሁከትም በርካታ ዜጎች መጎዳታቸውንና ንብረቶች ላይም ጉዳት መድረሱ ያነሱት የደህንነት እና ሲቪል ጥበቃ ሚኒስትሩ ይህንን መሰል ሁከትና ብጥብጥ እንዲያበቃ ለማድረግ መንግስት ይሰራል ብለዋል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ከተቃዋሚ ወገኖች የተሰጠ ማብራሪያ በሲጅቲኤን ዘገባ አልተካተተም፡፡በጊኒ ከምርጫ በኋላ በተፈጠረ ሁከት 7 ሰዎች ተገድለዋል፡፡