ከ38 የምርጫ ግዛቶች የ37ቱ የተቆጠረ ሲሆን ፕሬዘዳንት ኮንዴ የ2.4 ሚሊዮን ህዝብ ድምጽ አግኝተዋል
ከ38 የምርጫ ግዛቶች የ37ቱ የተቆጠረ ሲሆን ፕሬዘዳንት ኮንዴ የ2.4 ሚሊዮን ህዝብ ድምጽ አግኝተዋል
የጊኒው ፕሬዘዳንት አልፋ ኮንዴ በመጀመሪያ ደረጃ ውጤት በከፍተኛ ልዩነት አሸንፈዋል፤ አመጽ ባስነሳው ተቃውሞና ጠንካራ በሆነው ምርጫ ውስጥ የሶስተኛ የስልጣን ዘመን አግኝተዋል፡፡
እስካሁን ከ38 የምርጫ ግዛቶች የ37ቱ የተቆጠረ ሲሆን ፕሬዘዳንት ኮንዴ የ2.4 ሚሊዮን ህዝብ ድምጽ ሲያገኙ ተቀናቃኛቸው ሴሉ ዳሊን ዲያሎ 1.26 ሚሊዮን ድምጽ አግኝተዋል፡፡
በመጀመሪያ ውጤት መደሰታቸውንና ሙሉ በሙሉ እንደሚያሽንፉ እርግጠኛ መሆናቸውን የኮንዴ ቃል አቀባይ ቲቦ ካማራ ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡
የኮንዴ ለሶስተኛ ጊዜ ለፕሬዘዳንትነት ለመወዳደር ያሳለፉት ውሳኔ ተደጋጋሚ ተቃውሞዎችን አስነስቶ ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኗል፤ በተኩስ ምክንያት ከምርጫው ጀምሮ 13 ሰዎች ሞተዋል፡፡
የኮንዴ ውሳኔ በምእራብ አፍሪካ ያሉ መሪዎች የዲሞክራሲን ሂደት እየጎተቱ ነው የሚል ትችት እየተነሳ ነው፡፡ በኮትዲቮር ባለፈው ወር ፕሬዘዳንት አላሳን ኦታር ለሶስተኛ ጊዜ ለመወዳደር ፍላጎት በማሳየታቸው ተመሳሳይ ተቃውሞ መነሳቱ ይታወሳል፡፡
ልክ እንደ ኦታራ ሁሉ ኮንዴ በቅርቡ የተካሄደው የህገመንግስት ህዝበ ውሳኔ የስልጣን ገደብን እንዲያራዝሙ አድርገዋል፡፡ ነገርግን ተቃዋሚዎች ስልጣን ላይ በመቆየት ህገመንግስት ጥሰዋል ሲሉ ይከሷቸዋል፡፡
ውጤቱን የተቃዋሚ መሪው አይቀበሉትም፡፡ዲያሎ በራሳቸው ባሰባሰቡት መረጃ መሰረት አሸንፊያለሁ ብለው አውጀዋል፡፡
ምርጫ ኮሚሽን በበኩሉ በጊኒ ከተካሄዱት ምርጫዎች ሁሉ ግልጽና ንጹህ ነበር በማለት ምርጫውን ተከላክለዋል፡፡