የጊኒው ጁንታ ሰልጣንን ወደ ሲቪል ለማሸጋጋር የሚያስችል “የሽግግር ቻርተር” ይፋ አደረገ
ቻርተሩ ህገ መንግስትን ማርቀቅ እና “ነጻ፣ዴሞክራሲያዊ እና ግልጽ”ምርጫ ማካሄድ የሚሉ አንኳር ጉዳዮችን አካቷል
ቻርተሩ ኮሎኔል ማማዲ ዱምቦያን የሽግግር መንግስቱ ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ የሚያደርግ ነው ተብሏል
የጊኒው ወታደራዊ ኃይል ሰልጣንን ወደ ሲቪል ለማሸጋጋር የሚያስችል “የሽግግር ቻርተር” ይፋ አደረገ፡፡
የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ጊኒ እየመራ የሚገኘውና በሌተናል ኮሎኔል ማማዲ ዱምቦያ የሚመራው ወታደራዊ ኃይል ሀገሪቱን ወደ ሲቪል አገዛዝ ይመልሳል የተባለለትን “የሽግግር ቻርተር” ይፋ አደረገ፡፡
በሀገሪቱ ቴሌቭዥን ጣብያ ይፋ የተደረገው የሽግግር ቻርተር በውስጡ ህገ መንግስትን ማርቀቅ እና “ነጻ፣ዴሞክራሲያዊ እና ግልጽ”ምርጫ ማካሄድ የሚሉ አንኳር ጉዳዮችን ማካተቱ ኤ.ኤፍ.ፒ ዘግቧል፡፡
በተጨማሪም ቻርተሩ በሽግግር መንግስቱ ፕሬዝዳንትና ወታደራዊ አዛዥ በሆኑት በሌተናል ኮሎኔል ማማዲ ዱምቦያ የሚመራ ብሔራዊ የልማት ኮሚቴ ፣ በጠቅላይ ሚኒሰትር የሚመራ መንግስት እና ብሄራዊ ሽግግር ምክር ቤት የሚያካትት ነው፡፡
አዲሱ ቻርተር ሽግግሩን ያስፈጽማሉ የተባሉት አራት ተቋማት መለየቱንም ነው የተገለጸው፡፡
ማንኛውም የነዚህ ተቋማት አባል በማናቸውም “ምርጫዎች ላይ መሳተፍ እንደሌለበትም ይደነግጋል ” ቻርተሩ፡፡የጊኒ ፖለቲካ ቀውስ የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) ዋና አጀንዳ ከሆነ ሰነባብቷል፡
ኢኮዋስ፡ በምዕራብ እፍሪካዊቷ ሀገር ጊነ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ ምርጫ እንዲካሄድ እንዲሁም በወታደራዊ ጁንታው ቁጥጥር ስር የሚገኙት ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴ እንዲለቀቁ ይፈልጋል፡፡
የአልፋ ኮንዴን በኃይል ከስልጣን መነሳት ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት እንዲሁም የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) ጊኒን ከአባልነት ማገዳቸው የሚታወስ ነው፡፡