የጊኒው ወታደራዊ መሪ ምዕራባዊያንን “እናስተምራችሁ ማለታችሁን አቁሙ” ሲሉ ወቀሱ
ኮለኔል ማማዲ ዱምቢያ የምዕራባዊን ዲሞክራሲ ሞዴል በአፍሪካ አይሰራም ብለዋል
በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን የያዙት ኮለኔል ማማዲ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር አድርገዋል
የጊኒው ወታደራዊ መሪ ምዕራባዊያንን “እናስተምራችሁ ማለታችሁን አቁሙ” ሲሉ ወቀሱ፡፡
ከሁለት ዓመት በፊት በጊኒ ስልጣን በሀይል የተቆጣጠሩት ኮለኔል ማማዲ ዶምቢያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እያካሄደ ባለው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር ካደረጉ መሪዎች መካከል አንዱ ናቸው፡፡
ምዕራብ አፍሪካዊቷ ጊኒ ወደ መጥፎ ሁኔታ እየገባች እያለ በወቅቱ በስልጣን ላይ የነበሩትን ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴን በሀይል ከስልጣን በማስወገድ ታድጌያለሁ ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በአፍሪካ ወታደራዊ መንግስት ግልበጣዎች ለምን ተበራከቱ?
ወታደራዊ የጊኒ መሪው አክለውም ምዕራባዊያን አፍሪካን እናስተምራችሁ ማለታቸውን እንዲያቆሙም አስጠንቅቀዋል፡፡
የምዕራባዊያን የዲሞክራሲ ሞዴል በአፍሪካ በሀይል የተጫነ ነው ያሉት ኮለኔል ማማዱ አፍሪካ ከምዕራባዊያን በተጫነባት የዲሞክራሲ ሞዴል እየተሰቃየች እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
አሁን ወቅቱ ምዕራባዊያን አፍሪካን እንደህጻን እናስተምራችሁ የሚል እይታቸውን የሚያቆሙበት ወቅት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ኮለኔል ማማዲ በጊኒ በመፈጸሙት መፈንቅለ መንግስት ምክንያት ከምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ እና አፍሪካ ህብረት አባልነት ታግዳለች፡፡
በአፍሪካ ባለፉት ሁለት ዓመታት ስምንት መፈንቅለ መንግስት የተፈጸሙ ሲሆን ሰባቱ የተሳኩ ሆነው ስልጣን በሀይል መቆጣጠር ችለዋል፡፡
ማሊ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ቻድ፣ ሱዳን፣ ኒጀር፣ ጊኒ እና ጋቦን የተሳካ መፈንቅለ መንግስት የተፈጸመባቸው ሀገራት ናቸው፡፡