የምርጫ ውጤቱ አከራካሪ ከሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ ብጥብጥ እንዳይፈጠር ተሰግቷል
በጊኒ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መራጮች ድምጽ እየሰጡ ነው
የ 82 ዓመቱ ለሦስተኛ ጊዜ በሚወዳደሩበት የጊኒ አወዛጋቢ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መራጮች ድምፃቸውን እየሰጡ ነው ፡፡
ቀድሞውንም በፖለቲካ ቀውስ የተከፋፈለችው የምእራብ አፍሪካዊቷ ሀገር አርብ ዕለት ታጣቂዎች በአንድ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ አንድ ከፍተኛ የጦር መኮንን ከገደሉ በኋላ የባሰ ውጥረት ውስጥ ገብታለች፡፡
ፕሬዝዳንት ኮንዴ በርካታ ትችቶችን ጆሮ ዳባ ልብስ ብለው በመተው የሕገ-መንግሥት ለውጥ በማድረግ ነው ለሶስተኛ ጊዜ በዕጩነት የቀረቡት፡፡ ዋነኛ ተፎካካሪያቸው ሁለት ጊዜ ተወዳድረው በእሳቸው የተሸነፉት ሴሉ ዳሌን ዲያሎ ናቸው፡፡
በምርጨጫ ቅስቀሳ ወቅት የተከሰቱ የጎሳ ግጭቶች ፣ የምርጫ ውጤቱ አከራካሪ ከሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ ብጥብጥ እንዳይፈጠር ከወዲሁ ስጋት እንዲፈጠር አመላካች መሆናቸው ተዘግቧል፡፡
የሀገሪቱ መንግሥት የፀጥታ ምክንያቶችን በመጥቀስ ከአንዳንድ የጎረቤት ሀገራት ጋር ከወዲሁ ድንበሮችን ዘግቷል፡፡
ወደ 5.4 ሚሊዮን መራጮች ድምጽ እንደሚሰጡ የሚጠበቅ ሲሆን ውጤቱ ለብዙ ቀናት ሳይገለጽ ሊቆይ ይችላል እንደ ቢቢሲ ዘገባ፡፡
እጩዎች በቀጥታ ለማሸነፍ ከ 50 በመቶ በላይ ድምፅ ማግኘት ያስፈልጋቸዋል ፤ ይህ ካልሆነ ደግሞ በአውሮፓውያኑህዳር 24 ቀን ሁለተኛ ዙር ምርጫ ይደረጋል፡፡
ጊኒ ከነፃነት በኋላ በአምባገነናዊ እና በወታደራዊ አገዛዝ ስር እንደቆየች ይገለጻል፡፡ ሰራዊቱ ዳግም ፖለቲካ ውስጥ ሊገባ ይችላል የሚል ስጋትም አለ፡፡
የመከላከያ ሚኒስትሩ አርብ ዕለት በሰጡት መግለጫ የተወሰኑ ወታደሮች ከዋና ከተማዋ ኮናክሪ በስተሰሜን አቅጣጫ በ 130 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ኪንዲያ ውስጥ ወደሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ በመግባት የካምፑን ኮማንደር ኮ/ል ማማዲ ኮንዴን መግደላቸውን ገልጸዋል፡፡
አንዳንድ ዘገባዎች ኮማንደሩን አንድ ወታደር እንደገደለ ቢያመለክቱም በኋላ ላይ ባለሥልጣናት በሰጡት መግለጫ ድርጊቱን በቁጥጥር ስር እንዳዋሉ እና ወንጀሉን የፈጸሙ ወታደሮችን ለመያዝ ፍለጋ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡