የኢምሬትስ ፕሬዝደንት የተሳተፉበት የጉጅራት ግሎባል ሰሚት በህንድ ተከፈተ
በ2023 የተመሰረተው የጉጅራት ጉባኤ ልምድ እና መረጃ ለመቀያየር የሚረዳ አለምአቀፍ መድረክ መሆን ችሏል ተብሏል
ፕሬዝደንት ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናሀያን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በበርካታ ዘርፎች ላይ በርካታ የመግባቢያ ሰነዶች ተፈራርመዋል
የኢምሬትስ ፕሬዝደንት የተሳተፉበት የጉጅራት ግሎባል ሰሚት በህንድ ተከፈተ።
በርካታ መሪዎች የተሳተፉበት 10ኛው የጉጅራት ግሎባል ሰሚት ወይም ጉባኤ በህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ተከፍቷል።
በጉባኤው መክፈቻ የተገኙት የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናሀያን በጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በተመሰረተው ጉባኤ ላይ መሳተፋቸው ኩራት እንደተሰማቸው ገልጸዋል።
በ2003 የተመሰረተው የጉጅራት ጉባኤ ልምድ እና መረጃ ለመቀያየር የሚረዳ አለምአቀፍ መድረክ መሆን ችሏል ተብሏል።
ጉባኤው ከፈረንጆቹ ጥር 10-12 እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ፕሬዝደንት ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናሀያን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ የኢንቨትመንት ትብብርን ጨምሮ በበርካታ ዘርፎች ላይ በርካታ የመግባቢያ ሰነዶች ተፈራርመዋል።
ሁለቱ መሪዎች በኢነርጂ እና በወደብ ልማት ጉዳይም በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።
የኢምሬትስ ዜና አገልግሎት (ዋም) እንደዘገው የሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ የህንድ ጉብኝት በሀገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሸፋን አግኝቷል።
ሚዲያዎቹ የሁለቱ ሀገራት ግንኙን ጥልቅ መሆኑን እና የጉባኤውን አስፈላጊት በፊት ገጻቸው ዘግበውታል።
የኢንዲያን ኤክስፕረስ ጋዜጣ እንደዘገበው ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ እና ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናሀያን በአህመድባድ ግዛት 15 ዲቂቃ የፈጀ የሶስት ኪሎ ሜትር ጉብኝት አደርገዋል።