ፑቲን አረብ ኢምሬትስ ሲደርሱ የከብር አቀባበል ተደርጎላቸወል
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ቬክ መካመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን ለይፋዊ የስራ ጉብንት አቡድሃቢ ለገቡት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በጦርነት እና በነዳጅ ጉዳይ መካከለኛው ምስራቅ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን ጉብኝታቸውን በዛሬው እለት በአረብ ኢምሬትስ የጀመሩ ሲሆን፤ አቡድሃቢ ሲደርሱም የክብር አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በዚህም የሩሲያን ፕሬዝዳንት ያዘው የአውሮፕላን የአረብ ኢምሬትስን የአየር ክልል ውስጥ ሲገባም የአረብ ኢምሬትስ የጦር ጄቶች አጅበዋቸዋል።
ፑቲን አቡ ድሃቢ ሲደርሱም 21 ጊዜ መድፍ የተተኮሰ ሲሆን፤ የአረብ ኢምሬትስ አየር ኃይል አክሮባቲክ ቡድንም በአየር ላይ በጭስ የሩሲያን ባንዲራ ቀለማት ሰርቷል።
እንዲሁም፤ ግመል ጋላቢዎች እና በፈረስ ላይ የተጫኑ መኮንኖች የተለያዩ ባህላዊ የአቀባበል ስነሰርዓቶችም ተደርገዋል።
በአቀባበሉ ላይም ላይ የአረብ ኤምሬትሰው ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ፕሬዚዳንት ፑቲንን "ውድ ጓደኛዬ" በማለት እንደጠሩና የሩስያ አቻቸውን እንደገና በማግኘታቸው ደስተኛ እንደሆኑ መናገራቸው ተገልጿል።
ፕሬዚዳንቱ በጉብኝታቸው በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በመካከለኛው ምስራቅ ስላለው ሁኔታ እንደሚወያዩ ክሬምሊን አስታውቋል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዓለም አቀፍ የእስር ማዘዣ ከወጣባቸው በኋላ የውጭ ሀገራት ጉዞን በእጅቁ የቀነሱ ሲሆን፤ አብዛኛውን ጊዜም የቀድሞ የሶቪዬት ህብረት አካል የነበሩ ሀገራትን ብቻ ሲጎበኙ ነበር።
ፑቲን ከእነዚህ ሀገራት ውጪ የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን ያደረጉት ባሳለፍነው ጥቅምት ወር በቻይና ነበር።