በአረቢያ ባህር የመርከብ እግታ መፈጸሙን ተከትሎ ህንድ የጦር መርከብ አሰማራች
ህንድ በአጠቃላይ በህንድ ውቅያኖስ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ በዋናነት የምትቆጣጠር ሀገር ነች
የህንድ የጦር መርከብ እና ሁኔታውን የሚከታተል የጦር ጄት ወደ ታገተችው መርከብ መላኩን የህንድ የባህር ኃይል አስታውቋል
በአረቢያ ባህር የመርከብ እግታ መፈጸሙን ተከትሎ ህንድ የጦር መርከብ አሰማራች።
የላይቤሪያ ሰንደቅ አላማ የምታውለበልብ መርከብ በአረቢያን ባህር መታገቷን ተከትሎ ህንድ የጦር መርከብ አሰማርታለች።
የህንድ የጦር መርከብ እና ሁኔታውን የሚከታተል የጦር ጄት ወደ ታገተችው መርከብ መላኩን የህንድ የባህር ኃይል አስታውቋል።
በሶማሊያ ጠረፍ ላይ በታገተችው ኤምቪ ሊላ ኖርፎልክ ላይ 15 የክሪው አባላት ወይም ሰራተኞች የሚያሳይ መረጃ በትናትናው እለት ማግኘቱን ባህር ኃይሉ ገልጿል።
የህንድ የባህር ኃይሉ ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው መርከቧ ለእግሊዝ የማሪታይም ትሬድ ድርጅት ከአምስት እስከ ስድስት የሚሆኑ የታጠቁ ኃይሎች ጥቃት እንዳደረሱባት መልእክት ልካለች።
መግለጫው የህንዷ አይኤንኤስ ቸናይ መርከብ ወደ ቦታው መላኳን እና የናቫል ጄት ወደ ታገተችው መርከብ በማብረር ግንኙነት ማድረግ ተችሏል ብሏል።
በቀጣናው ፍጥጫ መጨመሩን ተከትሎ የህንድ የባህር ኃይል የሚያደርገውን ቅኝት አጠናክሮ ቀጥሏል።
ባህር ኃይሉ በዚህ ዚህ ሳምንት መጀመረመያ ላይ በሰሜን እና በማዕከላዊ የአረቢን ባህር በርካታ አሳ የማጥመድ እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን ገልጾ ነበር።
ህንድ በአጠቃላይ በህንድ ውቅያኖስ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ በዋናነት የምትቆጣጠር ሀገር ነች።