ጥናቱ አንድ ሰው የሚያረጅበትን ፍጥነት በ6 አመታት ማዘግየት የሚችሉ ሰባት የጤና ልምጆችን አግኝቷል
የእርጅና ፍጥነትን ሊያዘገዩ የሚችሉ ልምዶች ምንድናቸው?
በቅርቡ ይፋ የሆነ አንድ ጥናት አንድ ሰው የሚያረጅበትን ፍጥነት በ6 አመታት ማዘግየት የሚችሉ ሰባት የጤና ልምጆችን አግኝቷል።
ሳይንቲስቶቹ ሰባቱ ልምጆች የልብ ጤንነትን እንደሚያሻሽሉ እና የስነህይወታዊ እርጅና ፍጥነትን እንደሚያዘገዩ ገልጸዋል። እንደጥናቱ ከሆነ ጥሩ የልብ ጤና ያላቸው ሰዎች እርጅናቸው በስድስት አመታት ይዘገያል።
የጥናቱ ከፍተኛ አዘጋጅ ኑር ማከራም "መሰረታዊ የሆኑ የህይወት ዘይቤዎችን በመከተል እና የልብ ጤናን ማሻሻል ለወደፊት ብዙ ጥቅሞች ያመጣል" ብለዋል።
ሌላው ባለሙያ ዶናልድ ልሎይድ ጆንስ የዚህ ጥናት ውጤት በአሜሪካ የልብ ማህበር ላይ መቅረቡን እና ይህም በቅደምተከተላዊ እና በስነህይወታዊ እድሜ መካከል ያለውን ግንኙነት ለመረዳት እንደሚረዳ አብራርተዋል።
በጥናቱ የተለዩት ሰባቱ ልምዶች የሚከተሉት ናቸው፦
ሲጋራ ማጨስ ማቆም
ጤናማና የተመጣጠነ ምግብ ማዘውተር
ጥሩ እንቅልፍ
የሰውነት እንቅስቃሴ ማዘውተር
ክብደትን መቆጣጠር
የደም ግፊት ከመደበኛው እንዳያልፍ ማድረግ
በደም እና በኮሌስትሮል ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ጤናማ ማድረግ