ፖለቲካ
የትዳር አጋሩን 'በመጥረቢያ' የገደለው ግለሰብ በእድሜ ልክ እስራት ተቀጣ
ግለሰቡ የሁለት ልጆቹን እናት የተለያየ የሰውነት ክፍሏን በመጥረቢያ በመምታት ህይወቷ እንዲያልፍ አድርጓል
ፍርድ ቤት ተከሳሹ ላይ ከእድሜ ልክ ፅኑ እስራት በተጨማሪ ህዝባዊ መብቶቹ እንዲሻሩ ወስኗል
የትዳር አጋሩን 'በመጥረቢያ' የገደለው ግለሰብ በእድሜ ልክ እስራት ተቀጣ።
ፍቃዱ ሽፈራው የተባለ ግለሰብ ባለቤቱን "በሌላ ወንድ እጠረጥርሻለሁ" በማለት በመጥረቢያ መትቶ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጉን ፖሊስ ተናግሯል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው ተከሳሹ ወንጀሉን የፈጸመው ጥቅምት 28፤ 2015 ዓ.ም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ቦታው አርሴማ አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡
ግለሰቡ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ገደማ የሁለት ልጆቹን እናት የተለያየ የሰውነት ክፍሏን በመጥረቢያ በመምታት ህይወቷ እንዲያልፍ አድርጓል፡፡
ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ በዋለው ችሎት፤ ተከሳሽ ፍቃዱ ሽፈራው ላይ ከእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ቅጣት በተጨማሪ ህዝባዊ መብቶቹ ለዘወትር እንዲሻር ውሳኔ አሳልፏል ።