ፖለቲካ
የመረጃ ጠላፊዎች የኔቶን ሚስጥራዊ መረጃዎች ለሽያጥ ማቅረባቸው ተገለፀ
ኔቶ የትኛውም የኔትዎርክ አውታሩ እንደተጣሰ የሚጠቁም ነገር እንዳላገኘ አስታውቋል
ጠላፊዎች ለሽያቅ ካቀረቡት ውስጥ “MBDA” የተባለ የሚሳዔል ስርዓት ይገኝበታል
የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን (ኔቶ) ሚኒስጥራዊ መረጃዎች በመረጃ መዝባሪዎች መጠለፉ ተሰምቷል።
የመረጃ ጠላፊዎቹ የኔቶን ሚስጥራዊ መረጃዎች በኦንላይ (ኢንተርኔት) ላይ ለሽያጭ ማቅረባቸውንም ቢቢሲ ይዞት በወጣው ዘገባ አስታውቋል።
በኦንላይን ለሽያጭ ከቀረቡ የኔቴ ሚስጥራዊ መረጃዎች መካከል የፓን-አውሮፓውያን መከላከያ አምራች ምርት የሆነውን “MBDA” ሚሳዔል ስርዓት ዝርዝር እንደሚገኝበት ተገልጿል።
የኔቶ ቃል አቀባይ ከመረጃ ጠለፋው ጋር በተያያዘ በሰጡት አስተያየት፤ የትኛውም የኔቶ የኔትዎርክ አውታር እንደተጣሰ የሚጠቁም ነገር የለም ብለዋል።
ሆኖም ግን የ“MBDA” ሚሳዔል አምራች አካ የሆነው የጣሊያን ኩባያ ለመረጃ መንታፊዎች መግቢያ ሊሆን ይችላል በሚል ተገምቷል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ማንነታቸው ያልታወቀ የመረጃ ጠላፊዎች ለተዘረፈው የኔቶ መረጃ 15 ሚትኮይን (320 ሺህ) የአሜሪካ ዶላር ጠይቀዋል።
ዋጋው እና ሌሎች ዝርዝሮች በፈረንሣይ የሳይበር ደህንነት እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የዜና ድረ-ገጽ በነሃሴ ወር መጀመሪያ ላይ ካወጣው መረጃ ጋር የሚመሳሰል ነው ተብሏል።