ሀማስ አሜሪካ "በፍልስጤም ህዝብ ላይ በሚደረገው ወረራ እየተሳተፈች" ነው ሲል ከሰሰ
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶ ባይደን አሜሪካ ከእስራኤል ጎን እንደምትቆም ጥቃቱን ባወገዙበት መግለጫቸው ተናግረዋል
የሀማስ ቃል አቀባይ ሀዜም ካሴም "እንቅስቃሴው ህዝባችንን አያስፈራውም፤ ህዝባችንን እና ቅዱስ መሬታችንን መከላከላችንን እንቀጥላለን" ብለዋል
ፍልስጤምን እያስዳደረ ያለው ሀማስ የአሜሪካን የባህር ኃይል የመላክ እርምጃ ተቃውሟል።
አሜሪካ የባህር ኃይል ወደ ሜዲትራኒያን ባህር በማስጠጋት "በፍልጤም ህዝብ ላይ በሚደረገው ወረራ እየተሳተፈች" ነው የሚል ክስ አቅርቧል።
የሀማስ ቃል አቀባይ ሀዜም ካሴም "እንቅስቃሴው ህዝባችንን አያስፈራውም፤ ህዝባችንን እና ቅዱስ መሬታችንን መከላከላችንን እንቀጥላለን" ብለዋል።
የአሜሪካ የላከችው ባህር ኃይል ቡድን ኑክሌር ተሸካሚ ኤርክራፍት እና ጋይድድ ሚሳይል መሸከም የምትችለውን ዩኤስኤስ ጀራሌድ አር. ፎርድ የተሰኘችውን ግዙፍ የጦር መርከብ ያካተተ ነው ተብሏል።
አሜሪካ በሌባኖስ ያለው ሄዝቦላህ እና ሌሎች ጸረ- አስራኤል የሆኑ ቡድኖችን ለመከላከል ብዙ የጦር ጀቶች ወደ መካከለኛው ምስራቅ እየላከች መሆኗም ተገልጿል።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶ ባይደን አሜሪካ ከእስራኤል ጎን እንደምትቆም ጥቃቱን ባወገዙበት መግለጫቸው ተናግረዋል።
ባይደን አሜሪካ፣ እራኤል የተቃጣበትን "የሽብር ጥቃት" ለመቀልበስ የምትፈልገውን ሁሉ እንድታሟላ ታደርጋለች ብለዋል።
እየተካሄደ ባለው ግጭት ዙሪያ፣ ከእራኤል ጋር የዲፕሎማት ለዲፕሎማት፣ የደህንነት ለደህንነት እና የወታደራዊ ለወታደራዊ ተቋማት ውይይት መደረጉን ፕሬዝደንቱ ባይደን ገልጸዋል።
አሜሪካን ጨምሮ በርካታ ምዕራባውያን ሀገራት የእስራኤልን "ራሷን ከጥቃት የመከላከል መብት" ሲደግፉ ሌሎች ሀገራት ደግሞ ሁለቱም አካላት ግጭት እንዲያቆሙ በመጠየቅ ገለልተኛ አቋም አንጸባርቀዋል።
የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት የተጀመረው ሀማስ ከሁለት ቀናት በፊት በከፈተው ጥቃት ምክንያት ነው።
ሀማስ በሺዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶችን በማስወንጨፍ እና በደቡባዊ እስራኤል ወደሚገኙ ድንበሮች ዘልቆ በመግባት በ50 አመታት ውስጥ ከባድ የተባለ ጥቃት አድሷል።
እስራኤል እየወሰደች ያለችው የአጸፋ ጥቃት በጋዛ በርካታ ሰዎች ሞተዋል። ጦርነቱ አሁንም ቀጥሏል።