በእስራኤል ጦርና በፍልስጤማውያን ተዋጊዎች መካከል በ7 ግንባሮች ውጊያ እየተደረገ ነው
ሃማስ ባሳለፍነው ቅዳሜ በእስራኤል ላይ ያለተጠበቀ እና ድንገተኛ ጥቃት መሰንዘረሩን ተከትሎ በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል የተጀመረው ጦርነት ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል።
በሃማስ ጥቃት እና በእስራዔል የአየር ድብደባ ከሁለቱም ወገኖች የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ ማለፉ ተነግሯል።
- የፍልስጤሙ ሃማስ ቡድን እስራኤል ላይ ለምን ጥቃት ከፈተ? ማወቅ ያለብን ነጥቦች
- በእስራኤልና ፍሊስጤም መካከል አዲስ ስለተቀሰቀሰው ጦርነት እስካሁን የምናውቀው…
የእስራኤል መከላከከያ ኃይል ዛሬ ባወጣው መረጃ መሰረት በሃማስ ጥቃት የሞቱ እስራኤላውኝ ቁጥር 700 የደረሰ ሲሆን፤ 2 ሸህ 150 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።
የፍልስጤም ባለስልጣናት በሰጡት መረጃ ደግሞ በእስራኤል የአየር ድብደባ የሞቱ ፍልስጤማውያን ቁጥር 413 መድረሱን እና ከ2 ሺ 300 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን አስታውቀዋል።
የእስራኤልና የማሃስ ጦርነት ምን ላይ ይገኛል?
ሃማስ ወደ እስራኤል የሚተኩሳቸውን ሮኬቶች ከ36 ሰዓታት በኋላ እንደ አዲስ የጀመረ ሲሆን፤ እስራኤልም በጋዛ የምትፈጽመውን የአየር ድብደባ ቀጥላበታለች።
አሁን ላይ ጦርነቱ በ7 ግንባሮች ቀጥሎ የተካሄደ ነው የተባለ ሲሆን፤ 100 ሺህ የእስራኤል ወታደሮች በምድረ ላይ ሊደረግ ለሚችል ዘመቻ በተጠንቀቅ ላይ ናቸው ተብሏል።
እስራኤል ጦር ሰድሮት ፖሊስ ጣቢያን መልሶ መቆጣጠሩን ያስታወቀ ሲሆን፤ አሁንም ቢሆን የጋዛ ግንብን ጨምሮ በርካታ ስፍራዎች በፍልስጤመውያን ተዋጊዎች እጅ ይገኛል።
እስራኤል በጋዛ የምትፈጽመውን የአየር ድብደባ የቀጠለች ሲሆን፤ በጋዛ የሚገኙ መኖሪያ ቤቶች በአየር ድብደባው መውደማቸው ተነሯል።
የሚባኖሱ ሄዝቦላህ በሼባ ፋርምስ የሚገኝ የእስራኤል ጦር ካምፕ ላይ ለደረሰው ጥቃት ኃፊነቱን እንደሚወስድ አስታውቋል። እስራኤልም ለሄዝቦላህ ጥቃት መልሽ መስጠቷን አስታውቃለች።