እስራኤል ለምድር ወረራ እየተዘጋጀሁ ነው ብላለች
ታጋቾችን ለመልቀቅ የተኩስ አቁም ስምምነት እንደሚያስፈልግ ሀማስ ገለጸ።
የሀማስ ባለስልጣን በጋዛ ታግተው የተወሰዱ ሰዎችን ለመልቀቅ የተኩስ አቁም ያስፈልጋል ብለዋል።
እስራኤል ለምድር ወረራ እየተዘጋጀሁ ነው ያለች ሲሆን፤ አሜሪካ እና የአረብ ሀገራት ዘመቻውን እንድታዘገይ እየወተወቱ ነው።
ሀገራቱን የንጹሀን ዜጎችን ህይወት የበለጠ አደጋ ውስጥ የሚጥል ይሆናል ሲሉ ተማጽነዋል።
ኮምመርሰንት የተሰኘው የሩሲያ ጋዜጣ ሞስኮን የጎበኙትን የሀማስ የልዑካን ቡድን አባልን ጠቅሶ እንደዘገበው በሀማስ ጥቃት ከእስራኤል የተወሰዱትን ታጋቾች ለማግኘት ጊዜ ያስፈልጋል።
"በደርዘኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውለናል። አብዛኛዎቹ ሲቪሎች ናቸው፣ እናም በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ፈልገን ለማግኘት እና ከዚያም እነሱን ለመልቀቅ ጊዜ እንፈልጋለን" ብለዋል።
እስካሁን አራት ታጋቾችን የለቀቀው ሀማስ ከጦርነቱ የመጀመሪያዎቹ ቀናት ጀምሮ "ሲቪል እስረኞችን" የመልቀቅ አላማ እንዳለው ተናግሯል።
ነገር ግን ይህንን ተግባር ለማጠናቀቅ "ረጋ ያለ ከባቢ" እንደሚያስፈልግ ተናግሯል።