ሀማስ 70 የሚሆኑ የእስራኤል ታጋቾችን የሚለቀው በምትኩ የአምስት ቀናት ተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ ነው
ሀማስ 70 የሚሆኑ የእስራኤል ታጋቾችን በመልቀቅ ጉዳይ እየተነጋገረ መሆኑን ገለጸ።
የሀማስ ወታደራዊ ክንፍ እንደገለጸው 70 የሚሆኑ የእስራኤል ታጋቾችን የሚለቀው በምትኩ የአምስት ቀናት ተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ ነው።
ሀማስ በ50 ከመታት ውስጥ በእስራኤል ላይ ከባድ እና ያልተጠበቀ ጥቃት በማድረስ ነበር ባለፈው ጥቅምት ወር 240 የሚሆኑ ሰዎችን አግቶ የወሰደው።
ሀማስ በትናንትናው እለት ለኳታር አደራዳሪዎች እንደተናገረው ከእስራኤል ጋር ለሚደረገው የአምስት ቀናት ተኩስ አቁም ስምምነት 70 የሚሆኑ ሴቶች እና ህጻናት ታጋቾችን ለመልቀቅ ዝግጁ ነው።
የሀማሱ አል ቃሳም ብርጌድ ቃል አቀባይ አቡ ኡባይዳ ሪከርድ ተደርጎ በተለቀቀ ድምጽ "ባለፈው ሳምንት የኳታር ወንድሞቻችን የጠላትን ሴቶች እና ህጻናት እንድንለቅ እና በምትኩ 200 ፍልስጤማውያን ህጻናት እና የታሰሩ 75 ሴቶች እንዲለቀቁ ጥረት ሲያደርጉ ነበር" ብሏል።
ቃል አቀባዩ ተኩስ አቁም በሙሉ ጋዛ የሚተገበር እና እርዳት እንዲደርስ የሚያስችል መሆን አለበት ብለዋል።
ሀማስ እስራኤልን የተደረሱ ስምምነቶችን ቀን በማጓተት እና ተግባራዊ ባለማድረግ ይከሳል።
ሀማስ እስራኤል በእግረኛ ጦር ወደ ጋዛ መግባት ስትጀምር ለንግግር ዝግጁ መሆኑን ገልጾ የነበረ ቢሆንም እስራኤል አልተቀበለችውም።
በጦርነቱ በጋዛ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ በመፈጠሩ ምክንያት ተመድ እና በርካታ ሀገራት የተኩስ አቁም ጥሪ ቢያቀርቡም ሀማስን ለማጥፋት እቅድ የያዘችው እስራአል ፈቃደኛ ሳትሆን ቀርታለች።