ሀማስ ከደቡብዊ ሊባኖስ ሆኖ የእስራኤል ወታደራዊ ይዞታዎችን እያጠቃ መሆኑን ገለጸ
ባለፈው ጥር ወር እስራኤል በቤሩት ባደረሰችው የአየር ጥቃት የሀማስን ምክትል የፖለቲካ መሪ ሳሌህ አል አሮሪን ገድላለች
የሀማስ ወታደራዊ ክንፍ አል ቃሳም ብርጌድ እንዳስታወቀው ከደቡባዊ ሊባኖስ ሆኖ በእስራኤል ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ በርካታ ሚሳይሎችን እስወንጭፋል
ሀማስ ከደቡብዊ ሊባኖስ ሆኖ የእስራኤል ወታደራዊ ይዞታዎችን እያጠቃ መሆኑን ገለጸ።
የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ሀማስ ከደቡባዊ ሊባኖስ በመሆን በእስራኤል ይዞታዎች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ገልጿል።
የሀማስ ወታደራዊ ክንፍ አል ቃሳም ብርጌድ በዛሬው እለት እንዳስታወቀው ከደቡባዊ ሊባኖስ ሆኖ በእስራኤል ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ በርካታ ሚሳይሎችን እስወንጭፋል።
በሰሜን እስራኤል የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያዎች የተሰሙ ቢሆንም የደረሰ ገዱት ስለመኖሩ ግን እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።
አብዛኛውን የሊባኖስ ክፍል የተቆጣጠረው የሄዝቦለ ታጣቂ ቡድን ከእስራኤል ጋር እየተዋጋ ላለው ሀማስ አጋርነቱን ማሳየቱ ይታወሳል።
የሀማስ ወታደራዊ እና የፖለቲካ አመራሮችም ወደ ሊባኖስ እንደሚመላለሱ ይገለጻል።
በዚህ ምክንያት እስራኤልም የሀማስ መሪዎችን በማስጠለል የምትከሰውን የሂዝቦላ ታጣቂ ቡድን ይዞታዎችን እና የሀማስ መሪዎችን በተደጋጋሚ በአየር እያጠቃች ነው።
ባለፈው ጥር ወር እስራኤል በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤሩት ከተማ ዳርቻ ባደረሰችው የአየር ጥቃት የሀማስን ምክትል የፖለቲካ መሪ ሳሌህ አል አሩሪን ገድላለች።
የሀማስ እና የሄዝቦላ የተኩስ ልውውጥ፣ የሀማስ እና እስራኤል ጦርነት ከተጀመረ ጊዜ ወዲህ ተባብሶ ቀጥሏል።
እስራኤል እና ሀማስ ለማድራደር የተደረገው ጥረትም አንዳቸው ሌላኛቸው ያቀረቡትን ቅድመ ሁኔታ ውድቅ እያደረጉ በመቀጠላቸው እስካሁን አልተሳካም።
ሀማስ በጋዛ ዘላቂ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና የእስራኤል ጦር ለቆ እንዲወጣ ይፈልጋል።
እስራኤል በአንጻሩ የጋዛን የጸጥታ ስራ በዘላቂነት መቆጣጠር ትፈልጋለች።
ሀማስ በጥቅምት ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል እየወሰደች ባለው የአየር እና የምድር ጥቃት ከ34ሺ በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጋዛ ጤና ባለስልጣናት ተናግረዋል።