የሀማስ መሪ እስማኤል ሀኒየህ ወደ ቴህራን ሊያቀኑ ነው ተባለ
ይህ ሀኒየህ ጦርነቱ ከተጀመረ ከባለፈው ጥቅምት ወዲህ በኢራን የሚያደርጉት ሁለተኛ ጉብኝታቸው ይሆናል
የሀማስ መሪ እስማኤል ሀኒየህ በዛሬው እለት የኢራን ባለስልጣናትን ለማግኘት ወደ ቴህራን እንደሚያቀኑ ተገለጸ
የሀማስ መሪ ከኢራን ባለስልጣናት ጋር ለመወያየት ወደ ቴህራን ሊያቀኑ ነው ተባለ።
የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት በጋዛ አስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ የሚጠይቀውን የውሳኔ ሀሳብ ካጸደቀ በኋላ የሀማስ መሪ እስማኤል ሀኒየህ በዛሬው እለት የኢራን ባለስልጣናትን ለማግኘት ወደ ቴህራን እንደሚያቀኑ ሮይተርስ ዘግቧል።
ኢራን ስድስት ወር ገደማ ሊሆነው በተቃረበው እና ለ32ሺ ፍልስጤማውያን ግድያ ምክንያት በሆነው ጦርነት ሀማስን ደግፋለች።
ይህ ሀኒየህ ጦርነቱ ከተጀመረ ከባለፈው ጥቅምት ወዲህ በኢራን የሚያደርጉት ሁለተኛ ጉብኝታቸው ይሆናል።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ናሰር ከናኒ ትናንት የጸደቀውን የውሳኔ ሀሳብ "ጥሩ እርምጃ" ነው ብለውታል።
"የበላጠ ወሳኙ ደግሞ የጸደቀውን የውሳኔ ሀሳብ ወደ ተግባር መቀየር ነው"ብለዋል ከናኒ።
ሀማስም የተመድን የውሳኔ ሀሳብ በበጎ መቀበሉን ገልጾ፣ ተኩስ አቁም ግን ዘላቂ መሆን አለበት ብሏል።
በተመድ የጸጥታው ምክርት የቀረበው የአስቸኳይ ተኩስ አቁም የውሳኔ ሀሳብ ሊጸድቅ የቻለው አሜሪካ ጽምጸ ተአቅቦ በማድረጓ ነው።
የእሰራኤል ዋነኛ አጋር የሆነችው አሜሪካ ከዚህ በፊት በተመድ የጸጥታው ምክርቤተ እና በጠቅላላ ጉባኤው ላይ የሚቀርቡ የውሳኔ ሀሳቦች ድምጽን በድምድ የመሻር መብቷን(ቬቶ) ተጠቅማ እንዳይጸድቅ ታደርግ ነበር።
በትናንትናው እለት ግን አሜሪካ ተአቅቦ በማድረግ ከእስራኤል ፍላጎት የተቃረነ አቋም አንጸባርቃልች።
በዚህ ምክንያት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከፍተኛ የእስራኤል የልኡካን ቡድን በዋሽንግተን ሊያደርገው የነበረውን የጉዞ እቅድ ዘርዋል።
አሜሪካ በእሰራኤል ድርጊት ከፍተኛ ብስጭት እንደተሰማት ገልጸለች።
"ይህ በጣም የሚያበሳጭ ነው። በራፋ ሰላለው ሁኔታ አማራጮችን ለመፈለግ የሚያስችል ውይይት እንድናካሂድ የሚያስችለንን የዋሽንግተን ጉዞ በመሰረዛቸው በጣም ተበሳጭተናል"ብለዋል የኃይትሀውስ ቃል አቀባይ ጆን ክርቢይ።
ክርቢይ እንደተናገሩት ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣናት ለስራ ጉብኝት አሜሪካ ከሚገኙት የእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር ዩአቭ ጋላንት ጋር በታጋቾች፣ በሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እና በራፋ ለንጹሃን ሊደረግ ስለሚገባው ከለላ ጉዳይ ተገናኝተው ይወያያሉ።
ክርቢይ አሜሪካ በተመድ ድምጸ ተአቅቦ ብታደርግም የአሜሪካ ፖሊሲ አልተቀየረም ብለዋል።
የአሜሪካ ባለስልጣናት እስራኤል በጋዛ ጉዳይ በምታራምደው ፖሊሲ ዙሪያ ያላቸውን ስጋት ማንሳታቸውን ይቀጥላሉ ሲሉ ክርቢይ ተናግረዋል።