ሩሲያ ሀማስ ታጋቾችን እንዲለቅ ጫና እንዳደረገችበት ገለጸች
ሀማስን ከምድረ ገጽ አጠፋለሁ የምትለው እስራኤል በጋዛ እያካሄደች ያለውን መጠነሰፊ ጥቃት ቀጥላቀታለች
ሩሲያ የሀማስ የልኡክ ቡድን በሞስኮ ጉብኝት ባደረገበት ወቅት ታጋቾችን እንዲለቅ ጫና እንዳረገችበት ገልጻለች
ሩሲያ ሀማስ ታጋቾችን እንዲለቅ ጫና እንዳደረገችበት ገለጸች።
ሩሲያ የሀማስ የልኡክ ቡድን በሞስኮ ጉብኝት ባደረገበት ወቅት ታጋቾችን እንዲለቅ ጫና እንዳረገችበት ገልጻለች።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሀማስ የልኡካን ቡድን መቀበሉን እና ሶስት ሩሲያውያንን ጨምሮ ታጋቾችን እንዲለቅ ጫና እንዳደረገበት በትናንትናው እለት ገልጿል።
ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚካሄል ቦግዳኖብ የሀማስ የፖለቲካ ቢሮ አባል የሆነውን አቡ ማርዙክን ተቀብለዋል።
"በውይይቱ ወቅት፣ በእስራኤል እና ፍልስጤም መካከል ያለው ፍጥጫ እና በጋዛ ሰርጥ የተፈጠረው አስከፊ የሰብአዊ ቀውስ የትኩረት ነጥብ እንደነበር" ሚስቴሩ በመግለጫው ጠቅሷል።
በሩሲያ በኩል ሀማስ ባለፈው አመት ጥቅምት ወር በእስኤል ላይ ጥቃት በመሰንዘር ያገታቸውን የሩሲያ ዜጎች ጨምሮ በፍጥነት እንዲለቀቁ ውይይት ተደርጓል ተብሏል።
ትናንት በወጣው ሌላ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦግዳኖቭ በሩሲያ ከእስራኤል አምባሳደር ሲሞና ሀልፐሪን ጋር ተወያይተዋል።
ሚኒስቴሩ እንደገለጸው ሩሲያ በተመድ የጸጥታው ምክርቤት ውሳኔ መሰረት የሚተገበር የመካከለኛው ምስራቅ መፍትሄን ትደግፋለች።
ባለፈው ህዳር ወር በኳታር አደራዳሪነት በተደረሰው የስድስት ቀን ተኩስ አቁም ወቅት በርካታ ታጋቾች የተለቀቁ ቢሆንም አሁንም 100 ገደማ ታጋቾች በሀማስ እጅ እንዳሉ ይገመታል።
ሀማስን ከምድረ ገጽ አጠፋለሁ የምትለው እስራኤል በጋዛ እያካሄደች ያለውን መጠነሰፊ ጥቃት ቀጥላቀታለች።