ሀማስ ተኩስ አቁሙ ተግባራዊ በተደረገበት የመጀመሪያው ቀን 24 ታጋቾችን ለቀቀ
ታጋቾቹ የተለቀቁት ሀማስ እና እስራኤል ጦርነቱ ከተጀመረ ከሰባት ሰምንታት በኋላ በጋዛ ተኩስ እንዲቆም መስማማታቸው ተከትሎ ነው
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ የመጀመሪያ ዙሩን ታጋቾች የማስለቀቅ ስራ አጠናቀናል ብለዋል
ሀማስ ተኩስ አቁሙ ተግባራዊ በተደረገበት የመጀመሪያው ቀን 24 ታጋቾችን ለቀቀ።
የሀማስ ተዋጊዎች የተኩስ አቁም ስምምነቱ ተግባራዊ መሆን በጀመረበት በትናንትናው እለት ሴቶችን፣ ህጻናትን እና የታይ የእርሻ ሰራተኞችን ጨምሮ 24 ሰዎችን መልቀቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ታጋቾቹ የተለቀቁት ሀማስ እና እስራኤል ጦርነቱ ከተጀመረ ከሰባት ሰምንታት በኋላ በጋዛ ተኩስ እንዲቆም መስማማታቸው ተከትሎ ነው።
ታጋቾቹ በአራት መኪና ተሳፍረው እና ስምነት የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማህበር(አይሲአርሲ) ስራተኞች ተከትለዋቸው ከጋዛ ወጥተው በራፋህ ማቋረጫ በኩል ለግብጽ ባለስልጣናት መሰጠታቸውን አይሲአርሲ ገልጿል።
ተኩሱ እንዲቆሞ ስታደራድር የነበረችው ኳታር እንደገለጸችው የተወሰኑ ጥምር ዜግነት ያላቸውን ጨምሮ 13 እስራኤላውያን፣ 10 የታይ እና የፍሊፕንስ ዜጎች ተለቀዋል። በእስራኤል ታስረው የሚገኙ 39 ፍልሴጤማውያን ሴቶች እና ህጻናት በደርድሩ መሰረት ተፈተዋል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ የመጀመሪያ ዙሩን ታጋቾች የማስለቀቅ ስራ አጠናቀናል ብለዋል።
ኔታንያሁ ሁሉንም ታጋቾች ለማስለቀቅ በቁርጠኝነት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
የተኩስ አቁም ስምምነቱ ለአራት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጊዜው እስከሚጠናቀቅ ተጨማሪ ታጋቾች ይለቀቃሉ ተብሏል።