የቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን “የእስራኤል ኔታንያሁ አሸባሪ’ ነው፤ ሃማስ አይደለም” አሉ
ቱርክ በእስራኤልን የሚገኙ አምባሳደሯን ወደ ሀገር ቤት ጠርታለች
ኤርዶጋን “ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ጋር ያለኝን ግንኙነት አቋርጫለሁ” ብለዋል
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን “የእስራኤል ጠቅኔታንያሁ አሸባሪ’ ነው፤ ሃማስ ግን አይደለም” አሉ።
ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ይህንን ያሉት ባሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ በሀገሪቱ በተደገረ ሰልፍ ላይ ሲሆን በዚሁ ጊዜም “እስራኤል በመካከለኛው ምስራቅ ያለች ወራሪ ሀገር ነች” ማለታቸውም ይታወሳል።
የቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን በትናንትናው አልት ባደረጉት ንግግር ደግሞ፤ “ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋር ያለኝን ግንኙነት አቋርጫለሁ”ማለታቸው ተስመቷል።
“ናታንያሁ አሁን ከዚህ በሏላ የምናናግረው ሰው አይደለም ከዝርዝር ውስጥ አውጥነተዋል” ማለታቸውንም የቱርክ መገናኛ ብዙሃን ኤርዶጋንን ንግግር ዋቢአድርገው ዘግበዋል።
ነገር ግን “ይህ ማለት ቱርክ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት እያቋረጠች ነው ማለት አይደለም” ያሉት ፕሬዝዳንቱ የቱርክ የስለላ ሃላፊ ከእስራኤል እና ከፍልስጤም ባለስልጣናት እንዲሁም ከሃማስ ጋር ግንኙነት እንዳለው አክለዋል።
ኤርዶጋን ጦርነቱ ሲያልቅ ቱርክ “ጋዛን እንደ ሰላማዊ የፍልስጤም ግዛት አካል አድርጎ ማየት እንደምትፈልግ ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ቱርክ በእስራኤል የሚገኙትን አምባሳደሯን ወደ ሀገር ቤት መጣራቷን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያስታወቀ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ በጋዛ ያለው የሰብዓዊ ቀውስ ነው ተብሏል።
እስራኤል ቀደም ብላ ከደህንነት ስጋት ጋር ተያይዞ በቱርክ የሚገኙ ዲፕሎማቶቿን ማስወጣቷ ይታወሳል።
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ከዚህ ቀደም ሐማስ ለፍልስጤማዊያን እና መሬት የሚታገል የነጻነት ድርጅት እንጂ ሽብርተኛ እንዳልሆነ መናገራቸው ይታወሳል።
የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሀን እስራኤልን የመጎብኘት እቅድ የነበራቸው ቢሆንም ጉብኝታቸውን ሰርዘዋል።