ሀማስ እስራኤል ጦሯን ከጋዛ ለማስወጣት ቁርጠኛ ካልሆነች ምንም አይነት ስምምነት እንደማያደርግ ገለጸ
ሀምዳን አክሎም አደራዳሪዎች እስራኤል በዘላቂ ተኩስ አቁም ዙሪያ ያላትን ጥርት ያለ አቋም እንዲያሳውቁ ጠይቀዋል
በአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የቀረበው በሶስት ምዕራፍ የተከፋፈለው የተኩስ አቁም ሀሳብ በመጀመሪያ ዙር ለስድስት ሳምንት የሚቆይ ተኩስ አቁም እንዲደደረግ ይጠይቃል
ሀማስ እስራኤል ጦሯን ከጋዛ ለማስወጣት ቁርጠኛ ካልሆነች ምንም አይነት ስምምነት እንደማያደርግ ገለጸ
እስራኤል ዘላቂ ተኩስ ለማቆም በግልጽ ቁርጠኝነቷን ካላሳየች እና ጦሯን ሙሉ በሙሉ ከጋዛ ካላስወጣች ሀማስ ምንምአይነት ስምምነት እንደማይፈጽም የፍልስጤሙ ቡድን ከፍተኛ ባለስልጣን በትናትናው እለት ተናግረዋል።
ከአሜሪካ እና ከግብጽ ጋር ሀማስ እና እስራኤልን እያደራደረች ያለችው ኳታር እስራኤል ስምምነት ለመድረስ የሚያስችል ሙሉ የመንግስት ድጋፍ ያለው አቋም ይዛ እንድትቀርብ አሳስባታለች።
የሀማስ ባለስልጣን ኦሳማ ሀምዳን ባስተላለፉት የቴሌቪዥን መልእክት "ለዘላቂ ተኩስ አቁም እና ለእስራኤል ከጋዛ ጠቅልሎ መውጣት ዋስትና የማይሰጥ ስምምነት ማድረግ አንፈልግም" ብለዋል።
ባለፈው አርብ እለት በአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የቀረበው በሶስት ምዕራፍ የተከፋፈለው የተኩስ አቁም ሀሳብ በመጀመሪያ ዙር ለስድስት ሳምንት የሚቆይ ተኩስ አቁም እንዲደደረግ ይጠይቃል። በዚህ ዙር የእስራኤል ጦር ብዙ ህዝብ ካለባቸው ከሁሉም የጋዛ አካባቢዎች እንዲወጣ እና አረጋውያን እና ህጻናትን ጨምሮ በሀማስ እጅ ያሉ የተወሰኑ ታጋቶችን በመቶዎች በሚቆጠሩ የፍልስጤም እስረኞች መለዋወጥ እንዲደረግ ሀሳብ ቀርቧል።
ፕሬዝደንት ባይደን እንዳሉት ከሆነ ሀማስ እና እስራኤል በመጀመሪያው ዙሪ በዘላቂነት ተኩስ በማቆም ጉዳይ ይደራደራሉ። በሁለተኛው ዙር ሁሉም በህይወት የቀሩ ታጋቾች እንደሚለቀቁ እና የእስራኤል ከጋዛ መውጣት እና ዘላቂ ተኩስ አቁም እንደሚጀመር ባይደን ገልጸዋል።
"እስራኤል የምትፈልገው ሁሉንም ታጋቾቿን ለማስለቀቅ ያለመ የአንድ ዙር ተኩስ አቁም ነው፤ ከእዚያ በኋላ በህዝባችን ላይ ጦርነቷን ትቀጥላለች"ብለዋል ሀምዳን።
ሀምዳን አክሎም አደራዳሪዎች እስራኤል በዘላቂ ተኩስ አቁም ዙሪያ ያላትን ጥርት ያለ አቋም እንዲያሳውቁ ጠይቀዋል።
አሜሪካ ሀማስ ይህን የተኩስ አቁም ስምምነት ሀሳብ የሚቀበለው ከሆነ እስራኤልም ትቀበላዋለች ሲሉ መናገሯ ይታወሳል።
ሶስተኛው ዙር በስምንቱ ወር ጦርነት የወደመችውን ጋዛ መልሶ ስለመገንባት የሚያወሳ ነው።
እስራኤል ይህን የተኩስ ኡቁም ሀሳብ እንደምትፈልገም ባይሆንም እንደምትቀበለው መግለጿ ይታወሳል።