አምስት የእስራኤል ጦር ወታደሮች በእስራኤል ታንክ ተኩስ መገደላቸው ተገለጸ
የእስራኤል ወታደሮች በስህተት የተገደሉት በጃባሊያ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ነው
እስራኤል በጋዛ ውስጥ ዘመቻ ከጀመረች ወዲህ የተገደሉ የእስራኤል ጦር ወታደሮችን ቁጥር 278 ደርሷል
አምስት የእስራኤል ጦር አባላት ከእስራኤል ታንኮች በተከፈተ ተኩስ በስህተት መገደላቸው የሀገሪቱ ጦር አስታወቀ።
የእስራኤል ጦር አባላት የተደገሉት በሰሜናዊ ጋዛ ውስጥ በወታደራዊ ዘመቻ ላይ እያሉ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፤ የእስራል ጦር ከሃማስ ጋር ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ አስከፊው አደጋ ስል ገልጾታል።
- የእስራኤል ዋነኛ የጦር መሳሪያ አቅራቢዎች እነማን ናቸው?፤ የትኞቹስ ማቅረባቸውን አቆሙ?
- የእስራኤሉ ጠ/ሚኒስትር የጦር የመሳሪያ ድጋፍ ከቆመ “በጥፍራችንም ቢሆን እንዋጋለን” አሉ
የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት እንዳመለካተው ከሆነ የእስራኤል ጦር አባላት የተደገሉት ሁለት የእስራኤል ታንኮች በጃባሊያ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ በሚገኝ ህንጻ ላይ ተኩስ መክፈታቸውን ተከትሎ ነው።
የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት በጉዳዩ ላይ በሰጠው መግለጫ፤ “በ202ኛው ሻለቃ ፓራትሮፐርስ ብርጌድ ውስጥ የሚያገለግሉ አምስት ወታደሮቼ በጃባሊያ ካምፕ ረቡዕ ምሽት በእኛ ሃይሎች በተከፈተባቸው ተኩስ መገደላቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።
በአካባቢው የነበሩ ሁለት የእስራኤል ታንኮች የሻለቃው ምክትል አዛዥ በሚጠቀሙበት ህንፃ ላይ ሁለት የታንክ መድፎችን መተኮሳቸውን መግለጫው አስታውቀዋል።
በታንክ ተኩሱም ከሞቱ የእስራኤል ወታደሮች በተጨማሪ ሰባት ወታደሮች ቆስለዋል የተባለ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ ሶስቱ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ተነግሯል።
አደጋውን ተከትሎም እስራኤል በጋዛ ውስጥ ጦሯን አስገብታ ዘመቻ ከጀመረች ወዲህ የተገደሉ የእስራኤል ጦር ወታደሮችን ቁጥር 278 አድርሷል ነው የተባለው።
የእስራኤል ጦር በሰሜን ጋዛ ወደሚገኘው በጃባሊያ የስደተኞች ካምፕ ተመልሰው የገቡት የሃማስ ወታደሮች በስፍራው እንደ አዲስ እየተደራጁ መሆኑን መረጃ ከደረሰው በኋላ ነው።
ካሳለፍነው ረቡዕ ወዲህም በጃባሊያ የስደተኞች ካምፕ እና በዙሪያው በሚገኙ የከተማዋ ክፍሎች ላይ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን የእስራኤል ጦርና የሃማስ ሃይሎች አስታውቀዋል።