ሀሪስ ክርስቲያኖች እና አረብ አሜሪካውያን ድምጽ እንዲሰጧቸው ተማጸኑ
ሀሪስ የመጨረሻ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻቸውን በታሪካዊው የጥቁር ቤተ ክርስቲያን እና አረብ አሜሪካውያን በሚበዙበት ሚችጋን ግዛት አካሂደዋል
ሮይተርስ እንደሰበሰበው የህዝብ አስተያየት ከሆነ መራጮች ሁለቱንም ፕሬዝደንታዊ እጩዎች አይወዷቸውም
የዲሞክራቷ ፕሬዝደንታዊ ኤጩ ካማላ ሀሪስ ክርስቲያኖች እና አረብ የሆኑ አሜሪካውን ድምጽ እንዲሰጧቸው ተማጽነዋል።
ባለፈው ቅዳሜ ሀሪስ የመጨረሻ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻቸውን በታሪካዊው የጥቁር 'ቸርች' ወይም ቤተ ክርስቲያን እና አረብ አሜሪካውያን በሚበዙበት እና ከፍተኛ ፉክክር በሚካሄድባት ሚችጋን ግዛት አካሂደዋል።
- ነገ ስለሚጀመረው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እስካሁን የምናውቀው
- ትራምፕ ምርጫውን አሸንፈው የዩክሬኑን ጦርነት ለማስቆም የሚሞክሩ ከሆነ ሊገደሉ እንደሚችል የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዝዳንት ተናገሩ
ተቀናቃኛቸው የሪፐብሊካን እጩ የሆኑት ትራምፕ ደግሞ በፔንስልቬንያ በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ የተስተጋቡ ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮችን ሲደግፉ ታይተዋል።
የህዝብ አስተያቶች እንደሚያሳዩት በሴት መራጮች የሚደገፉት ሀሪስ እና በሂስፓኒክ መራጮች የማደገፉት ትራምፕ ከፍተኛ ፉክክር ውስጥ መግባታቸውን ያሳያል።
ሮይተርስ እንደሰበሰበው የህዝብ አስተያየት ከሆነ መራጮች ሁለቱንም እጩዎች እንደማይወዷቸው ቢገልጹም፣ ድምጽ ከመስጠት እንደማያግዳቸው ተናግረዋል።
እንደ ፍሎሪዳ ዩኒቨርሲቲ የምርጫ ላብ መረጃ ከሆነ እስካሁን ከ78 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት አሜሪካውያን ከማክሰኞው የምርጫ ቀን ቀደም ብለው ድምጽ ሰጥተዋል። ይህ ቁጥር በ100 አመታት የአሜሪካ ታሪክ ውስጥ በ2020 ምርጫ ከፍተኛ ሆኖ የተመዘገበውን የ160 ሚሊዮን መራጭ ግማሽ ሊሆን እየተቃረበ ነው።
በማክሰኞው ምርጫ ሁለሁም በኩል ኮንግረሱን ለመቆጣጠር አሁንም እድሎች አሉ።
ሪፐብሊካኖች በሴኔት አብላጫ መቀመጫ መያዝ የሚችሉበት እድል ያለ ሲሆን ዲሞክራቶች ደግሞ ሪፐብሊካን በተወካዮች ምክርቤት ያላቸውን ጠባብ ብልጫ የመቀየር ከፍ ያለ እድል አላቸው ተብሏል።
ፓርቲያቸው ሴኔት እና የተወካዮች ምክርቤትን መቀጣጠር የማይችሉ ፕሬዝደንት ትልልቅ ውሳኔዎችን ለማጸደቅ ይቸገራሉ።
"በሁለት ቀናት ውስጥ ለሚመጣው ትውልድ የሀገራቸውን እጣ ፈንታ የመወረን ኃይል አለን" ሲሉ ሀሪስ በዴትሪዮት በሚገኘው 'ግሬተር ኢማኑኤል ኢንስቲትዩሽናል ቸርች ኦፍ ጎድ' ተገኝተው ለአማኞች ተናግረዋል።
"እርምጃ መውሰድ አለብን። መጸለይ ብቻ በቂ አይደለም፤ ማውራት ብቻ በቂ አይደለም።"
ትራምፕ ግን ይህን ምርጫ እንደሚያሸንፉ በእርግጠኝነት እየተናገሩ ናቸው። ትራምፕ ምርጫውን የምሸነፈው እንደ 2020ው ማጭበርበር ከተፈጸመ ብቻ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
ዲሞክራቶች በአንጻሩ ትራምፕ ጽምጽ ቆጠራው ሳይጠናቀቅ ትራምፕ በሀሰት አሸንፌያለሁ ብለው ሊያውጁ ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል።