ካማላ ሀሪስ በይፋ የዲሞክራት ፕሬዝደንታዊ እጩ ሆኑ
ካማላ ሀሪስ የዲሞክራት እጩ ለመሆን የበቁት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን፣ ከእጩነት ራሳቸውን ማግለላቸውን ተከትሎ ነው
የዲሞክራት ፓርቲ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው 99 በመቶ የሚሆኑት ተወካዮች ድምጻቸው ለሀሪስ ሰጥተዋል
ካማላ ሀሪስ በይፋ የዲሞክራት ፕሬዝደንታዊ እጩ ሆኑ።
ስደተኞች ቤተሰቦች የተገኘችው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንት ካማላ ሀሪስ በትናንትናው እለት የዲሞክራት ፕሬዝደንታዊ እጩ መሆናቸው ይፋ ሆኗል።
ሀሪሰ ይፋዊ የዲሞክራት ፓርቲ ፕሬዜደንታዊ እጩ ለመሆን ከተወካዮች በቂ ድምጽ ማግኘታቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል። ሀሪስ እጩ ለመሆን ከ4000 ተወካዮች ውስጥ የ1976ዎቹ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የነበረ ሲሆን ከተጠበቀው በላይ አግኝተው እጩ መሆናቸው ተገልጿል።
የሀሪስ እጩነት ይፋ የሆነው የዲሞክራት ናሽናል ኮንቬንሽን ተወካዮች በኦለንላይ አማካኝነት ያደረጉት የአምስት ዙር ምርጫ በትናንትናው እለት ከተጠናቀቀ ካደረጉ በኋላ ነው።
የዲሞክራት ፓርቲ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው 99 በመቶ የሚሆኑት ተወካዮች ድምጻቸው ለሀሪስ ሰጥተዋል።
ካማላ ሀሪስ የዲሞክራት እጩ ለመሆን የበቁት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን፣ ከእጩነት ራሳቸውን ማግለላቸውን ተከትሎ ነው።ባይደን ከእጩነት ራሳቸውን ማግለላቸውን ባሳወቁበት መግለጫቸው ሀሪስ የዲሞክራት ፕሬዝደንታዊ እጩ እንዲሆኑ ድጋፋቸውን መስጠታቸው ይታወሳል።
በቅርቡ የተሰበሰቡ የህዝብ አስተያየቶች ከትራምፕ ይልቅ ሀሪስ በበርካታ ግዛቶች የተሻለ ድጋፍ እንዳላቸው አሳይተዋል።
ነገርገን ትራምፕ፣ ባይደን ከእጩነት ማግለላቸውን ካሳወቁ በኋላ ከባይደን ይልቅ ሀሪስ ለማሸነፍ እንደሚቀሏቸው ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ሀሪስ፣ ለሁለት ምዕተ አመት በዘለቀው የዲሞክራሲ ታሪኳ ሴት ፕሬዝደንት ሆና በማታውቅበት እና የአፍሪካ ዝርያ ያለው ፕሬዝደንት በተመረጠበት ሀገር፣ ለኃይት ሀውስ የሚወዳደሩ የመጀመሪያዋ ጥቁር እና እስያዊት አሜሪካዊ ለመሆን በቅተዋል።