የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከምርጫ ፉክክክር ራሳቸውን አገለሉ
ከዴሞክራች ጫና ሲደረግባቸው የነበረው ባይደን በመጨረሻም ራሳቸውን ከፉክክሩ ውጪ አድርገዋል
ለፓርቲዬ እና ለሀገሬ ስል ከድጋሚ ምርጫ ውድድር ራሴን አግልያለሁ ብለዋል
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከ2024 የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ከምርጫ ፉክክክር ራሳቸውን አገለሉ።
ፕሬዝዳንቱ በሀገራዊ እና አለምአቀፋዊ መድረኮች ላይ በተደጋጋሚ ከሚፈጽሙት ስህተት ባለፈ በቅርቡ በተካሄደው የመጀመርያ ዙር የምርጫ ክርክር ሀሳባቸውን በተገቢው መንገድ ለመግለጽ ሲቸገሩ ታይተዋል፡፡
ይህን ተከትሎም በክርክሩ በተቀናቃኛቸው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ብልጫ እንደተወሰደባቸው በመግለጽ የዴሞክራት ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች ፕሬዝዳንቱ ከእጩነት እንዲነሱ ሲጠይቁ ቆይተዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳነት ጆ ባይደን ዛሬ ማምሻውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው በለቀቁት መግለጫ ላይ “ለፓርቲዬ እና ለሀገሬ ጥቅም ሲባል” ራሴን ከ2024 ፕሬዝዳንተዊ የምርጫ ፉክክር አውጥቻለው” ብለዋል።
“እምነቱን ለጣለብኝ ለአሜሪካ ሕዝብ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ” ያሉት ፕሬዝዳንት ባይደን፤ “ዛሬም ሆነ ሁልጊዜ አሜሪካውያን ከተባበሩ ምንም ነገር ማድረግ አያቅታቸውም ብዬ አምናለሁ።
ፕሬዝዳንት ባይደን ከምርጫው ፉክክር ለመውጣት መወሰናቸውን በተመለከተ በሚቀጥለው ሳምንት ለአሜሪካ ሕዝብ ንግግር እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል።
ባይደን ራሳቸውን ማግለላቸው ተክተሎም ምክትላቸው ካማላ ሃሪስ እሳቸውን ተክተው ለፕሬዝዳንት እንዲወዳደሩ እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል።
“ድንቅ አጋር” በማለት ምክትላቸው ካማላ ሃሪስን ያወደሱት ፕሬዝዳነት ጆ ባይደን፤ ካማላ ሃሪስን በእርሳቸው ቦታ ለፕሬዝዳንትነት እንዲቀርቡ እንሚፈልጉ አስታውቀዋል።
ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ የዴሞክራት ፓርቲ እጩ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲቀርቡም ባይደን ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።