ልዩልዩ
በአሜሪካ በዶሮዎችን ጸብ ምክንያት የሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ
በሀዋይ አውራ ዶሮዎችን እርስ በርስ ማፋለም እና ከተመልካቾች ገቢ መሰብሰብ የተለመደ ነው
በሀዋይ የአውራ ዶሮዎችን ጸፍልሚያ ይከታተሉ በነበሩ ሰዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ሁለት ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል
በአሜሪካ በዶሮዎችን ጸብ ምክንያት የሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።
በአሜሪካዋ ሀዋይ ግዛት ውስጥ የዶሮዎች ፍልሚያ ሰዎች በተሰበሰቡበት ማካሄድ የተለመደ ነው።
ከሶስት ቀናት በፊት እስከ 200 ሰዎች ይከታተሉት በነበረ የዶሮ ፍልሚያ ውድድር ላይ በተፈጠረ ግጭት ሁለት ሰዎች ሲሞቱ ሶስት ሰዎች ደግሞ ከባድ የአካል መጉደል አጋጥሟቸዋል ተብሏል።
እንደ ኤፒ ዘገባ ከሆነ ግድያውን ፈጽመዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ የተያዙ ሲሆን ለግጭቱ ምክንያት እስካሁን ይፋ አልሆነም።
በሀዋይ አውራ ዶሮዎችን እርስ በርስ ማፋለም እና ከተመልካቾች ገቢ መሰብሰብ የተለመደ ቢሆንም የሀገሪቱ ህግ ግን ይህንን እንደማይፈቅድ ተገልጿል።
በአሜሪካ ህዝብ በተሰበሰበባቸው ስፍራዎች ላይ ተኩስ መክፈት እየጨመረ የመጣ ሲሆን በ2022 ብቻ ከ30 ሺህ በላይ አሜሪካዊያን ህይወታቸውን አጥተዋል።
የአሜሪካ ፖለቲከኞች ለሟቾች ቁጥር መጨመር የጦር መሳሪያ ቁጥጥሩ ዝቅተኛ መሆኑን በዋና ምክንያትነት በመጥቀስ ህጉ እንዲጠብቅ በማሳሰብ ላይ ናቸው።
ሁሌ ምርጫ በደረሰ ቁጥርም የጦር መሳሪያ ህግ ጉዳይ ዋነኛ አጀንዳ በመሆን ይታወቃል።