ትዊተር በኩባንያው አበዳሪዎች ሚሊዮን ዶላሮች እንዲከፍል ክስ ካቀረቡበት በኋላ ቀውስ እንደገጠመው ይነገራል
በአሜሪካ በሺዎች ለሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች የትዊተር አገልግሎት መቋረጡ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥን የሚከታተለው ዳውን ዳውንተር ድረ-ገጽ አስነብቧል፡፡
አሁን ላይ 4ሺህ 500 ተጠቃሚዎች ትዊትር መጠቀም እንዳልቻሉም ሮይተርስ ድረ-ገጹ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
ትዊተር በጉዳዩ ላይ የሰጠው ምላሽ አልሰጠም።
ባለቤትነቱ የቢሊየነሩ ኢሎን መስክ የሆነው ትዊተር በታህሳስ ወር ተመሳሳይ የአገልግሎት መቋረጥ ችግር ገጥሞት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በአለም ዙሪያ ያሉ ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን ለማግኘት ተቸግረው እንደነበር አይዘነጋም፡፡
ኩባኒያው ባለፈው ወር ባጋጠመው ሌላ የአገልግሎት መቋረጥም ከ8ሺህ በላይ በሚሆኑ ተጠቃሚዎች ላይ ተጽእኖ ፈጥሮ እንደነበር አይዘነጋም፡፡
ትዊተር በኩባንያው አበዳሪዎች 14 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት መዋጮ እንዲከፍል የሚጠይቁ በርካታ ክስ ካቀረቡበት በኋላ ቀውስ እንደገጠመው ይነገራል፡፡
እንደ "ቢዝነስ ኢንሳይደር" መረጃ ከሆነ ትዊተር በአሁኑ ወቅት ከወለድ በተጨማሪ ብዙ ደረሰኞችን ባለመክፈሉ ምክንያት ቢያንስ 9 እዳዎች እንዲከፍል የሚጠይቁ ክስ ቀርቦበታል፡፡
ኢሎን መስክ ባለፈው ጥቅምት ወር የኩባንያውን ፕሬዝዳንትነት ከተረከበ በኋላ በትዊተር ላይ ክስ ሲመሰረት ይህ የመጀመሪያው አይደለም።
ትዊተርን ካበደሩ ኩባንያዎች መካከል አንዱ ካናሪ ኤልኤልሲ የተባለ የግብይት ኩባንያ ሲሆን የኤሎን ማስክ ኩባንያ 392,239,000 ዶላር ያልተከፈለ ሂሳብ መክፈል አልቻለም ሲል ከሷል።