ቅርንፉድ በሶዲየም፣ ካልሺየም፣ ብረት እና ፎስፎረስ መበልጸጉ ለጸጉር እድገትና ጤና ወሳኝ ድርሻ እንዲኖረው አድርጎታል
ለቆዳ ጤና ወሳኝ ድርሻ ያለው፣ የምግብ መፈጨትን የሚያፋጥነው፣ የአፍ ጠረንን መልካም የሚያደርገው ቅርንፉድ፥ ተዘርዝሮ የማያልቅ ጥቅሞች አሉት።
በኢትዮጵያውያን የአመጋገብ ስርአት ትልቅ ስፍራ ያለው ቅርንፉድ ለጸጉር እድገትም ትልቅ አበርክቶ አለው። ብዙዎችን ለሚያስቸግረው ፎረፎርም ሆነ የጸጉር ሽበት የቅርንፉድ ቅባትን መጠቀም ይመከራል።