የሱዳን ጦር አመራሮች ከተቀየሩ በ72 ሰዓት ውስጥ የሰላም ስምምነት ለማድርግ ዝግጁ ነን- ሃሜቲ
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ መሪ ለቀጠለው ግጭት የሱዳን ህዝብን ይቅርታ ጠይቀዋል
ሄሚቲ የሱዳን ጦር ለሦስት አስርት ዓመታት በስልጣን ላይ ከነበሩት ታማኞች ትዕዛዝ እየተቀበለ ነው ሲሉ ከሰዋል
የሱዳን ጦር አመራር ከተቀየር በ72 ሰዓት ውስጥ የሰላም ስምምነት ለማድርግ ዝግጁ መሆናቸውን የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መሪ ጄኔራል መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ ተናገሩ።
ጄኔራል መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሚቲ) ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በካሜራ ብቅ ብለው የጦሩ መሪዎች እንዲለወጡ ጠይቀዋል።
በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በማበረዊ ትስስር ገጽ የተለቀቀው ቪዲዮ፤ ጄኔራል መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሚቲ) ለቀጠለው ግጭት የሱዳን ህዝብን ይቅርታ ጠይቀዋል።
"ጦር ኃይሎች ላሉ ወንድሞቻችን አፋጣኝ መፍትሄ ከፈለጋችሁ፤ አመራራችሁን ቀይራችሁ በ72 ሰዓት ውስጥ ስምምነት ላይ እንደርሳለን" ብለዋል።
ሃሜቲ በሰራዊታቸው ተከበው ባስተላለፉት 5 ደቂቃ በሚረዝመቀው የቪዲዮ መልእክታቸው፤ በሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች ዝርፊያ እየፈጸሙ ነው መባሉን አስተባለዋል።
ሄሜዲ ከዚህ ቀደም ባሰራጯቸው የድምጽ መልዕክቶች ሰራዊቱን ለሦስት አስርት ዓመታት ያህል በስልጣን ላይ ከነበሩት ታማኞች ትዕዛዝ እየተቀበለ ነው ሲሉ ከሰዋል።
የሱዳን ጦር እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ወደ ሲቪል አገዛዝ ለመሸጋገር በተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ ባለፈው ሚያዝያ ወር ግጭት ገብተዋል።
በጦርነቱ ከሦስት ሚሊዮን በላይ ዜጎች የተፈናቀሉ ሲሆን፤ ሀገሪቱንም ክፉኛ የሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ ወድቃለች።
በዋና ከተማይቱ ካርቱም ቢያንስ 580 ንጹሀን ዜጎች ተገድለዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።