የሽምግልና ሙከራ ያልተሳካለት የሱዳን ጦርነት 100ኛ ቀኑን ያዘ
በሳምንቱ መጨረሻ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ከካርቱም በስተደቡብ በሚገኙ አካባቢዎች መንቀሳቀስ፤ ከጦር ኃይሉ የአየር ጥቃት ገጥሞታል
ተፋላሚ ወገኖች ሀገሪቱን ወደ ዲሞክራሲ ለማሸጋገር የተያያዘ እቅድ ላይ ተለያይተዋል
ጦርነቱ የቀጠለበት የሱዳን ግጭት 100ኛ ቀኑን እሁድ ሲደፍን፤ በአንዳንድ ክፍሎች ግጭት ተቀስቅሷል።
የቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ኃይሎች የሽምግልና ሙከራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ለመጣው ግጭት መውጫ መንገድ ማግኘት አልቻሉም።
ሚያዚያ 15 በሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በስልጣን ሽኩቻ ጦርነቱ ፈንድቷል።
ከ700 ሽህ በላይ ሰዎች ወደ ጎረቤት ሀገሮች መሰደድን ጨምሮ ከሦስት ሚሊዮን በላይ ተፈናቅለዋል።
ጤና ጥበቃ ሚንስቴር በጦርነቱ አንድ ሽህ 136 ሰዎች ተገድለዋል ብሏል። ምንም እንኳን ባለስልጣናት ቁጥሩ ከዚህ ከፍ ያለ ነው ብለው ቢያምኑም።
ጦር ሰራዊቱም ሆነ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ድል መቀናጀት ባይችሉም፤ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በዋና ከተማይቱ ካርቱም የበላይ ነው ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ጦርነቱ ወደ ምዕራብ በተለይም በግጭት ሲናጥ ዓመታትን ወዳሳለፈው የዳርፉር ክልል በመስፋፋቱ በዋና ከተማው ውስጥ ያሉ መሰረተ ልማቶች እና አስተዳደሮች ፈርሰዋል።
በሳምንቱ መጨረሻ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ከካርቱም በስተደቡብ በሚገኙ አካባቢዎች ተንቀሳቅሷል። በጦር ኃይሉ የአየር ጥቃት እንደተፈጸመባቸው እማኞች ገልጸዋል።
ከሀገሪቱ ትላልቅ ከተሞች አንዷ በሆነችው ኒያላ እና የደቡብ ዳርፉር ዋና ከተማ ከሀሙስ ጀምሮ በመኖሪያ አካባቢዎች ግጭቶች መቀጠላቸውን እማኞች ተናግረዋል። በአካባቢዎቹ ቢያንስ 20 ሰዎች መሞታቸውን የህክምና ምንጮች ገልጸዋል።
ለሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች በተደጋጋሚ የተኩስ አቁም ስምምነት ያስገኙ ንግግሮችን እንደገና ለመጀመር በጂዳ ልዑካን ልከዋል።
በፈረንጆቹ 2019 የቀድሞ ገዥ ኦማር አልበሽር ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ፤ የሰራዊቱ መሪዎች እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የጋራ ምክር ቤቱን መርተዋል።
ሀገሪቱን ወደ ዲሞክራሲ ለማሸጋገር የተያያዘ እቅድ ላይ ተለያይተዋል።