የኬንያው ፕሬዝዳንት ጦራቸውን ይዘው መጥተው ከሱዳን ጦር ጋር መፋለም ይችላሉ- የሱዳን ጦር አመራር
የኬንያው ፕሬዝዳንት የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል ወደ ሱዳን ገብቶ ሰላም እንዲያስከብር ሀሳብ አቅርበዋል
ፕሬዝዳንት ሩቶ ለፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ያደላሉ የሚል ወቀሳ ከሱዳን ጦር ተደጋግሞ ተሰምቷል
ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከፈለገ የኬንያን ጦር ይዞ መጥቶ ከሱዳን ጦር ጋር መፋለም ይችላል ዲሉ የሱዳን ጦር አመራር ተናገሩ።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያን ሩቶ የሚመሩት የኢጋድ መፍትሄ አፈላላጊ ቡድን በቅርቡ በአዲስ አበባ ባደረገው ስብሰባ የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል ወደ ሱዳን እንዲገባ ምክረ ሀሳብ አቅርቧል።
ይህንን በተመለከተ ትናንት አስተያየት የሰጡት የዱዳን ጦር ተጠባባቂ ኢታማዦር ሹም ሌተናል ጄነራል ያስር አል አታ ሀሳቡን ተቃውመውታል።
ሌተናል ጄነራል ያስር አል አታ በሱዳን ጦር ስር ለሚገኘው የልዩ ዘመቻ እዝ ባደረጉት ንግግር ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ የሚለውን ነገር መተው አለበት ሲሉ አሳስበዋል።
ሌተናል ጄነራል ያስር አል አታ አክለውም ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከፈለገ ተጠባባቀከ ሃይል የሚለውን ትቶ የከየንያን ጦር ይዞ በመምጣት ከሱዳን ጦር ጋር መፋለ፦ ይችላል ሲሉም ተናግረዋል።
የሱዳን ጦር የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ለፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ያደላሉ የሚል ወቀሳ በተደጋጋሚ ሲያቀርብባቸው ቆይቷል።
ጦሩ ኬንያ "የሱዳን ግጭት የሁለት ጄኔራሎች ፍልሚያ ነው" ማለቷን በጽኑ እንደሚቃወም ሲገልጽ ተደምጧል።
የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የመረጣቸው የአራት ሀገራት መሪዎች በአዲስ አበባ በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ሲመክሩም ጦሩ ተወካዩን ወደ አዲስ አበባ ልኮ የነበረ ቢሆንም ፕሬዝዳንት ሩቶ የምክክሩ መሪነታቸው ካልተቀየረ አልሳተፍም ብለው በስብሰባው ላይ ሳይገኙ መቅረታቸው የሚታወስ ነው።