ሩዘሳባጊና የተባሉት ግለሰብ የጽንፈኛ ታጣቂ ቡድኖች መስራችና ድጋፍ ሰጭ ነበሩ በሚልነው የተከሰሱት
ሩዘሳባጊና የተባሉት ግለሰብ የጽንፈኛ ታጣቂ ቡድኖች መስራችና ድጋፍ ሰጭ ነበሩ በሚልነው የተከሰሱት
በሩዋንዳ በፈረንጆቹ 1994 የተካሄደውን ዘርማጥፋት አስመልክቶ በተሰራው የ“ሆቴል ሩዋንዳ”ፊልም ላይ እንደ ጀግና የተወደሱት ፓል ሩዘሳባጊናን በሽብር ክስ መያዟን አስታውቋለች፤ በካቴና በማሰር በሚዲያ ፊትም አቅርባዋለች፡፡
ሩዘሳባጊና ለኦስካር በታጨው የሆቴል ሩዋንዳ ፊልም ላይ የሆተል ስራ አስኪያጅ ሆኖ ሲሰራ እንዴት ከሁቱ ሰዎች ጋር በመገናኘት ቱሲዎችን ከጥቃት ሲከላከል እንደነበረ ያሳያል፡፡ በዛሬው እለት ሁለት የፖሊስ አባላት የ66 አመቱን ሰው በሩዋንዳ የምርመራ ቢሮ ባዘጋጁት መግለጫ ላይ በማቅረብ ሚዲያዎች እንዲቀርጹ አድርገዋል፡፡
የፊት ማስክ የለበሱት ሩዘሳባጊና ምንም አልተናገሩም፡፡ ከዚህ በፊት ግን በተራ ፕሮፓጋንዳ ምክንያት ሰለባ መሆኑን ገጸዋል፡፡ ሩዘሳባጊና የጽንፈኛ ታጣቂ ቡድኖች መስራችን ድጋፍ ሰጭ ናቸው፤ ከሀገር ውስጥና ከውጭ በተለያየ መልኩ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ነበር የሚል ክስ ነው የቀረባቸው፡፡
የምርመራ ቢሮው ቃል አቀባይ ቴሪይ ሙራንጊተራ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት ሩዘሳባጊና የሽብርና የገንዘብ ሽብርን ጨምሮ በርካታ ክስ ይመሰረትባቸዋል ብለዋል፡፡
ቢሮው በትዊተር ገጹ እንደጻፋ ሰውየው በአለም አቀፍ ትብብር አማካኝነት መያዙን አስታውቋል፡፡ሩዘሳባጊና የሩዋንዳው ፕሬዘዳንት ፖል ካጋሜ ተች እንደነበሩና ከሩዋንዳው ዘር ማጥፋት በኋላ ከሀገር ውጭ እንደነበሩ አንዲሁም በፈረንጆቹ 2005 ከአሜሪካን ትልቅ ሽልማት አግኝተው ነበር፤ በዚህም አለምአቀፋዊ ጭብጨባ ተበርክቶላቸው ነበር፡፡
ነገርግን በሀገር ውስጥ ንዴትን በማስከትለ ሌላ የጀኖሳይድ እያንዣበበ ነው፤ይሄኛው ግን ቱሲዎች በሁቶዎች ላይ ነው፡፡
በሩዋንዳ በፈረንጆቹ 1994 በተካሄደው የዘር ማጥፋት በ100 ቀናት ውስጥ 800ሺ ቱሲዎችና ለዘብተኛ ሁቱዎች ተጨፍጭፈው ተገድለው ነበር፡፡ ጭፍጨፋው የቆመው የቱሲ አማጺ መሪ ፖል ካጋሜ ስልጣን በመቆጣጠራቸው ነበር፡፡